ዊልያም ሼክስፒር

ኢንጊሊዛዊ የሆነው ገጣሚና ትያትር ጸሀፊ ዊልያም ሼክስፒር በኤፕሪል 23 1564 አ.ም ስታንፈርድ በምትባል ከተማ ተወለደ ። ምንም እንኳን አባቱ ስኬታማ ነጋዴ ቢሆኑም ሼክስፒር በዩኒቨርሲቲ መማሩን የሚገለልጽ ምንም ማስረጃ የለም ። ግን በስታንፈርድ አዲሱ የንጉሥ ትምህርት ቤት የክላሲካል ላቲን ትምህርት ተምሯል በመባል ይነገራል ። 

ገና የ18 አመት ልጅ እንደነበረ በእድሜ የምትበልጠውን አን ሃሰዌን አገባት ። ከአንም 2 ሴት ልጆችና አንድ ወንድ ልጅ ወለዱ ። ሀምኔት የተባለው ወንድ ልጃቸው ግን የ11 አመት ታዳጊ እያለ በልጅነቱ ሞተ።

ሼክስፒር ከቤተሰቦቹ ርቆ በለንደን ከተማ ግጥሞቹን በመጻፍና ትያትሮቹ ላይ በመስራት አብዛኛው ጊዜውን ያሳልፍ እንደነበር ይታወቃል ። ይሄም ሊመቻችለት የቻለው በ1605 አካባቢ የገዛው ንብረት የገበያ ዋጋው እጥፍ ሊሆን በመቻሉ ነበር። 

የሼክስፒር አብዛኞቹ የቀድሞ የትያትር ስራዎች አስቂኝ ከነበሩት እንደ “ኤ ሚድሰመርስ ናይት ድሪም” እና ታሪክ ላይ ያጠነጠኑ እንደ “ሄንሪ አምስተኛ” ይጠቀሳሉ ። 

በቀድሞ 17ኛው ክፍለ ዘመን ሼክስፒር ትያትሮቹን የትራጀዲ ወይም አሳዛኝ ታሪኮች ላይ በማተኮር ሀምሌት ፣ ኦቴሎ ፣ ሮምዮና ጁሊየት እና ንጉሥ ሊር የተባሉትን አበርክቷል ። 

ከሼክስፒር ምርጥ ስራዎች መካከልም ይካተታሉ ። ባጠቃላይ ሼክስፒር በህይወት ዘመኑ 38 የሚጠጉ ትያትሮችን ጽፏል።

በግጥም ዙሪያ ደግሞ 154 የሚሆኑ ስራዎችን አቅርቦ እነዚህን ስራዎቹ አብዛኛው ባልተሳኩ የፍቅር ታሪኮች ላይ ያተኮሩ ሲሆን በማራኪ የቋንቋና ቃላት አጠቃቀሙ በግጥሞቹ የብዙዎችን አድናቆት ለማግኘት አስችሎታል ። የሼክስፒር ትያትሮች በኢንጊሊዘኛ ስነ-ጽሁፍ ከሌሎች ጸሃፊዎች ይበልጥ በጥልቅ የተጠኑ ሲሆን ወደ በርካታ ቋንቋዎችም ለመተርጎም በቅተዋል ። ምንም እንኳን ሼክስፒር ከብዙዎች ለትያትር ስራዎቹ የላቀ ምስጋና ቢያገኝም በተቃራኒም ከብዙ ሰዎች ሙግትም ያጋጥመው ነበር ።  ለዚህም ምክኒያት የነበረው የመደበኛ ትምህርት ምሩቅ ባለመሆኑ እንደ ምክኒያት ይጠቀሳል።

ሼክስፒር እንደ ተዋናይ ፣ ጸሃፊ እና በድራማ ድርጅት ባለቤትነት ህየወቱን ያሳለፈ የአለም ታላቅ የድራማ ሰው በመባል ይታወቅ ነበር ። ሼክስፒር “የዕድሜ ሳይሆን ለሁሉም ዘመን” ሲል ቤን ጆንሰን ይገልጻዋል ። ሼክስፒር ለኢንጊዘኛ ቋንቋ ወደ 3000 ሚጠጉ ቃላትን ያበረከተ ታላቅ ጸሃፊ እነደሆነም ይታወቃል። 

የሼክስፒር አሟሟት ግልጽ ባይሆንም በ52 አመቱ አካባቢ ከድሬይተን እና ቤን ጆንሰን የተባሉ ጓደኞቹ ጋር በነበረበት ወቅት ቀድሞ በያዘው ትኩሳት ምክኒያት ህይወቱ እንዳለፈ ይነገራል።  

1 thought on “ዊልያም ሼክስፒር”

Comments are closed.