የሆድ ድርቀት

የሆድ ድርቀት እነዚህ ድርቀት ምልክቶች ናቸው:: የደረቀ ወይንም የጠነከረ ሰገራ መጠኑያነሰ ሰገራ ሰገራ ለመውጣት ሲያስቸግር በሳምንት ውስጥ ከሶስት ወይንም ከዛ ያነሰ ጊዜ ሰገራ መውጣት ሲኖር ናቸው:: የሆድ ድርቀት መነሻ ሊሆን የሚችለው ከአንጀት ችግር ከአመጋገብ ልምድ የተነሳ የመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳቶች ድርቀት ስጋት ሊሆን የሚችለው መቼ ነው? ከሰገራ ጋር ደም መቀላቀል ወይንም ከተጠቀሙ በኋላ ደም የመፍሰስ ትኩሳት ሲኖር የክብደት መቀነስ የምግብ ፍላጎት ማጣትና ድካም ሲኖር ድርቀት ሲፈጠር ምን ላድርግ? የቃጫነት መጠናቸው የበዙ ምግቦችን ማለትም አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን አብዝቶ መመገብ ጠዋት ጠዋት እንደነ ሻይና ቡና ያሉ መጠጦችን መጠጣት ውሃ በብዛት መጠጣት ሰገራ የመምጣት ስሜት ሲኖር ወዲያውኑ ወደ ሽንት ቤት መሄድ (ለረጅም ጊዜ አፍኖ አለመቆየት) መቼ ወደ ሐኪም ቤት ልሂድ? ቀደም ሲል ከነበረው የሰገራ አወጣጥ ፀባይ መለየት ወይንም አዲስ ድርቀት መከሰት ድርቀት እየተመላለሰ ከሶስት ሳምንት በላይ ከቆየ ድርቀት እንዳይፈጠር ለመከላከል ምን እናድርግ? ቃጫነት የበዛባቸውን ምግቦችን በብዛት መመገብ ጠዋት ላይ ሻይ ወይንም ቡና መጠጣት ውሃና ሌሎች ፈሳሾችን በብዛት መጠጣት በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት ሽንት ቤት መጠቀም/ሰገራ መውጣት

የጉሮሮ ሕመም

የጉሮሮ ሕመም በቫይረስ ወይም በባክቴሪያ ኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት ሲሆን እነዚህ ቫይረስና ባክቴሪያዎች በአፍና በአፍንጫችን አድርገው በመግባትም ጭምር የጉሮሮ ሕመምን ያስከትላሉ፡፡ የጉሮሮ ሕመም በቫይረስ ወይም በባክቴሪያ ኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት ሲሆን እነዚህ ቫይረስና ባክቴሪያዎች በአፍና በአፍንጫችን አድርገው በመግባትም ጭምር የጉሮሮ ሕመምን ያስከትላሉ፡፡ የጉሮሮ ሕመም ምልክቶች ምንድን ናቸው? የጉሮሮ መከርከር ለመዋጥ መቸገር ትኩሳት ሳል የራስ ምታት የምግብ ፍላጎት መቀነስ የድካም ስሜት መሰማት ብርድ ብርድ ማለት በጆሮና ባንገት አካባቢ ሕመም መሰማት በአንዳንድ ሰዎች ላይ ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች በተጨማሪ ማቅለሽለሽ ማስመለስ መጥፎ የአፍ ጠረን የድምፅ መለወጥ አፍን ለመክፈት መቸገር ሊኖሩ ይችላል የጉሮሮ ሕመም ሕክምና ሕመሙን እንዳስከተለው ተህዋስያን ዓይነት ይለያያል፡፡ በቫይረስ ምክንያት የሚመጣን የጉሮሮ ሕመም ሰውነታችን ባለው የበሽታ መከላከል አቅም የሚዋጋ ሲሆን መድኃኒት መውሰድ አስፈላጊ አይሆንም፡፡ በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰትን የጉሮሮ ሕመም ሕክምና ቦታ በመሄድ ባክቴሪያ አጥፊ መድኃኒቶችን (Antibiotics) መውሰድ ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሕመሙን ሁኔታ እንዲያስታግስልን፤ በቂ ዕረፍት መውሰድ ትኩስ ፈሳሽ መውሰድ፡- ሻይ፤ወተት፤አጥሚት ለስለስ ያሉ ምግቦችን መመገብ፡- ሾርባ ለብ ባለ ውሃ በጨው እና በዝንጅብል መጉመጥመጥ ሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መውሰድ ጠቃሚ ነው፡፡

የሽንት ኢንፌክሽን

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምንድን ነው? የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የምንለው ከኩላሊት እስከ የውሃ ሽንት ማስወገጃ ጫፍ ድረስ የሚከሰተውን የኢንፌክሽን ዓይነት ነው. በአብዛኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሚያጠቃው የውሃ ሽንት የሚከማችበት እና ፊኛ በመባል የሚታወቀውን የአካላችን ክፍል ነው. በሴቶች ተፈጥሮአዊ የሆነ የሽንት ቧንቧ ጫፍ ማጠር ምክንያት ከወንዶች ይልቅ ተጠቂነታቸው እንደሚጨምር ጥናቶች ያሳያሉ. ሕመምን የመከላከል አቅማቸው የቀነሰ እንደ የስኳር ሕመምተኞችና እርጉዝ ሴቶች ላይም በብዛት ይከሰታል. ቧንቧ ኢንፌክሽን እንዴት ሊከሰት ይችላል የሽንት? ባክቴሪያ ከሽንት ማስወገጃ ጫፍ ወደላይኛው የሽንት ቧንቧ አካል ይገባል. ይህም ሊከሰት የሚችለው በአካባቢው የሚገኘው የሠገራ ማስወጫ በባክቴሪያ የተበከለ ስለሆነ ነው. በመሆኑም በምንፀዳዳበት ጊዜ የግል ንጽህናን ባለመጠበቅ (ባለመታጠብ) በግብረሥጋ ግንኙነት ጊዜ በተለያየ ምክንያት ሽንትን ለማስወገድ የሽንት ቱቦ በሚገባበት ወቅት ሊከሰት ይችላል. የኩላሊት ጠጠር እና የፕሮስቴት እጢ ያሉት ሕመሞች ደግሞ ተፈጥሮአዊ የሆነውን የውሃ ሽንት አወጋገድን በማስተጓጎል ለኢንፌክሽን ሊዳርጉ ይችላሉ. በደም ውስጥ የሚገኝ ባክቴሪያም ይህንን ኢንፌክሽን ሊያስከትል ይችላል. ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክቶች ምንድን ናቸው የሽንት? የውሃ ሽንት በምንሳወግድበት ጊዜ የማቃጠል ስሜት መሰማት የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት ከእንብርት በታች የሕመም ስሜት መሰማት ደም የቀላቀለ ወይንም መጥፎ ጠረን ያለው ሽንት መኖር ትኩሳትና ብርድ ብርድ የማለት ስሜት መሰማት የማቅለሽለሽ ስሜትና ማስመለስ ናቸው እነዚህ ምልክቶች በተለይ የስኳር ሕመምተኛ; እርጉዝ ሴት; የኩላሊት ሕመም ተጠቂ የሆኑ እና በእድሜ በገፉ ሰዎች ላይ ከተከሰቱ ጊዜ ሳይሳጡ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ያስፈልጋል ቧንቧ ኢንፌክሽንን እንዴት መከላከል ይቻላል የሽንት? በብዛት ፈሳሽ መውሰድ ባክቴሪያ በሽንት ቧንቧ ውስጥ እንዳይቀመጥ በማድረግ ይከላከላል. ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በኋላ እና ከተፀዳዱ በኋላ የግል ንጽሕናን መጠበቅ ተገቢ ነው.

የስኳር በሽታ

ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የስኳር ሕመም ምልክቶች: የስኳር ሕመምን በተመለከተ በተለያዩ የጤና ምክር መስጫ ፕሮግራሞች ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤ የማስጨበቻ ሥራዎች እየተሰሩ ናቸው፡፡ ከዚህ በታች ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የሕመሙን ጠቋሚ ምልክቶች እንግራችኋለሁ፡፡ ስለስኳር ሕመም በዝርዝር በቅርቡ የሚያስገባችሁ ይሆናል፡ ከተለመደው ጊዜ በተለይ ውሃ መጠማትና በተደጋጋሚ የውኃ ሽንት መምጣት፡፡ የስኳር ሕመም ለኩላሊት ችግር በማጋለጥ ቀዳሚ ደረጃን የሚይዝ ሲሁን በደምውስጥ የሚገኝ የስኳር መጠን መጨመር የኩላሊት ሥራ ያዛባል፡፡ የድካም ስሜት መሰማት የስኳር ሕመም ከፍተኛ የድካም ስሜትን ያስከትላል፡፡ የሰውንት ክብደት መጨመር በራሱ ለስኳር ሕመም ከማጋለጥ ባለፈ የድካም ስሜት እንዲበረታ ያደርጋል፡፡ የዓይን ችግር ማናኛውም ዓይነት የዓይን ችግር የስኳር ሕመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ጊዜ ሳይሰጡ ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የስኳር ሕመምተኞች ለግላውኮማ የመጋለጥ ዕድላቸው ስለሚጨምርና በካታራክት (በዓይን ሞራ) ሊጠቁ ስለሚችሉ የዓይን ሕመም ከተሰማ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ይመከራል፡፡ የእግር መደንዘዝ የስኳር ሕመም የነርቭ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ ይህም ጉዳት በአብዛኛው የሚከሰተው በእጃችንና በእግራችን ላይ ባሉ ነርቮች ላይ ነው፡፡ በነርቭ ወይንም በደም ሥር ላይ የሚደርስ ጉዳት የእግር መደንዘዝ ቀጥሎም የሕመም ስሜትን ያስከትላል፡፡ ሕመሙ በጊዜ ብዛት እየባሰ የሚሄድ ሲሆን መጠጥ እና ሲጋር ማጨስ ሕመሙን ያባብሰዋል፡፡ የቆዳ ላይ ኢንፌክሽንና በቶሎ የማይድን ቁስለት የስኳር ሕመም ቆዳችንን ጨምሮ ማንኛውንም የሰውነት ክፍላችንን ሊጎዳ ይችላል እንዲያውም የስኳር ሕመም ያለበት ሰው በቀላሉ በባክቴሪያ እና በፈንገስ የሚመጣ ለቆዳ ላይ ኢንፌክሽን ያጋልጣል እነዚህም ኢንፌክሽኖች ቁስለትን ያስከትላሉ በቶሎ ሊድኑም አይችሉም፡፡ ምንጭ፡-- በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም

የኩላሊት ጠጠር

የኩላሊት ጠጠር ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳይ መቆየት የሚችል ሲሆን ከኩላሊት ተነስቶ በሽንት ማስወገጃ መስመር እስከ ፊኛ ድረስ ሊያደርግ በሚችለው ጉዞ ምክንያት ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡ የኩላሊት ጠጠሮች ጠጣር የሆኑ ትናንሽ ዝቃቾች ሲሆኑ የተሰሩትም ከሚኒራል እና ከአሲድ ሶልት ነው፡፡ የኩላሊት ጠጠሮች በሽንት ቧንቧ መስመር ማለትም ከኩላሊት እስከ ፊኛ ድረስ የማጥቃት ባሕሪም አላቸው፡፡ የኩላሊት ጠጠር ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳይ መቆየት የሚችል ሲሆን ከኩላሊት ተነስቶ በሽንት ማስወገጃ መስመር እስከ ፊኛ ድረስ ሊያደርግ በሚችለው ጉዞ ምክንያት ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡ የኩላሊት ጠጠር ሕመም ምልክቶች ምንድን ናቸው? ከፍተኛ የጎን የሕመም ስሜት እና ከጎድን አጥንት በታች የጀርባ ሕመም ስሜት ከፍተኛ የሕመም ስሜት ወደ ንፍፊትና ወደ ታችኛው የሆድ ክፍል የሚሰራጭ የውኃ ሽንትን በምናስወግድበት ወቅት የሚኖር ከፍተኛ የሕመም ስሜት የውኃ ሽንት ቀለም ለውጥ(ቀይ፣ቡኒ ወይንም ሮዝ) የደፈረሰ ወይንም መጥፎ ጠረን ያለው የውኃ ሽንት አጣዳፊ የውኃ ሽንት መኖር የውኃ ሽንት ከሌላው ጊዜ በተለየ መብዛት ተያያዥ የሆነ ኢንፌክሽን የሚኖር ከሆነ ለምሳሌ ትኩሳትን ብርድ ብርድ ማለት መኖር በኩላሊት ጠጠር ምክንያት የሚከሰት ሕመም ቦታውን ሊቀያይር ይችላል፡፡ይህም የሚሆነው ጠጠሩ በሽንት ቧንቧ መስመር ውስጥ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ነው፡፡ ሐኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው? - ከታች የተጠቀሱትን የሕመም ምልክቶች ከተመለከቱ ወደ ሐኪም በአፋጣኝ መሄድ የኖርብዎታል፡፡ እነዚህም፡ ከፍተኛ የሕመም ስሜት የሚሰማዎ ከሆነ ከፍተኛ የሕመም (የውጋት) ስሜት ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ካለ ትኩሳትና ብርድ ብርድ ስሜት ካለዎት ደም የቀላቀለ የውኃ ሽንት ሲኖር የውኃ ሽንት ማስወገድ ካቃተዎ ለኩላሊት ጠጠር ሕመም ተጋላጭንት የሚዳርጉ ሁኔታዎች ጎልማሳ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች ከ40 ዓመትና ከዚያ በላይ ያሉ ሰዎችን ያጠቃል ወንድ ፆታ ለኩላሊት ጠጠር ሕመም ተጋላጭነትን ይጨምራል የአመጋገብ ሁኔታችን ለምሳሌ ከፍተኛ መጠን ያለው የፕሮቲን፣ ጨው እና ስኳር መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭነትን ይጨምራል በቂ የፈሳሽ መጠን አለመውሰድ ለኩላሊት ጠጠር መፈጠር ዋነኛ ምክንያት ነው፡፡ የሰውነት ክብደት በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ከሆነ እና የመሳሰሉት ተጋላጭነትን ይጨምራሉ፡፡ የኩላሊት ጠጠርን እንዴት መከላከል ይቻላል? በቀን ውስጥ የሚወስዱትን የፈሳሽ መጠን ይጨምሩ፡፡ የሚያስወግዱት የውኃ ሽንት መጠንም 2.5 ሊትር እንዲሆን ይመከራል፡፡ የአመጋገብ ልምድዎን መቀየር የጨው መጠን እና የፕሮቲን መጠናቸው የበዛ ምግቦችን ማስወገድ ናቸው፡፡ የኩላሊት ጠጠር ሕክምና ምንድን ነው? የኩላሊት ጠጠር ሕክምና እንደጠጠሩ ዓይነት እና መጠን ይለያያል፡፡ የጠጠሩ መጠን አነስተኛ ከሆነ የቀዶ ጥገና ሕክምና አስፈላጊ ላይሆን ይችላል፡፡ በቂ ፈሳሽ በመውሰድ (3 ሊትር) በቀን መውሰድ ጠጠሩ ከውኃ ሽንት ጋር ተቀላቅሎ እንዲወጣ ይረዳል፡፡ ሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መውሰድ አነስተኛ ጠጠሮች ስለሚያስከትሉ ሕም ማስታገሻ መጠቀም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ሐኪምዎ ጡንቻዎችን የሚያፍታታ መድኃኒትም በመስጠት ጠጠሩ ከውኃ ሽንት ጋር ተቀላቅሎ እንዲወጣ እንዲረዳዎ ሊያደርግ ይችላል፡፡ የጠጠሩ መጠን ትልቅ ከሆነ ሐኪምዎ የተለያዩ ጠጠሩን የማስወገጃ መንገዶችን የሚያማክርዎ እና የሚያስረዳዎ ይሆናል፡፡ ስለዚህም ሐኪምዎን በሚገባ ማማከር ተገቢ ነው

መጥፎ ትንፋሽ

መጥፎ የአፍ ጠረን(ሃሊቶስስ) የአፍን ንፅህና በደንብ ካለመጠበቅ የሚከሰት ችግር ቢሆንም ሌሎች የአፍና የጥርስ ንፅህና ቢጠበቅም ለህክምና አስቸጋሪ የሆኑ መንስኤዎችም አሉት፡፡ ይህ ሁኔታ ሲከሰት ከማስጨነቁም በላይ የታማሚዉን ሁለንተናዊ ግንኙነት (በትዳርም ይሁን በሌሎች ግንኙነቶች፤በስራ ቦታ) ሊጎዳ ይችላል፡፡ መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጡ ከሚችሉ መንስኤዎች ዉስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ፡፡ የአፍ ንፅህናን ያለመጠበቅ የድድ ህመም መኖር ሽታ ሊያመጡ የሚችሉ ባክቴሪያዎች በአፍና የአንጀት ክፍሎች ዉስጥ መራባት እንደ ካንዲዲያስስ ያሉ የፈንገስ ህመሞች መከሰት የሳይነስ እንፎክሽን መድኃኒቶች(በተለይ አፍን የሚያደርቁ መድሃኒቶች) ሲጋራ ማጨስ የተወሱ የምግብ አይነቶች(ነጭ ሽንኩርት፤ሽንኩርት፤ሰርዲን፤ከፍተኛ የገንቢ ምግብ(ፕሮትን) ያላቸዉ ምግቦች) የምግብ ያለመፈጨት ችግርና የጉበት ችግር የሆድ ድርቀት መጥፎ የአፍ ጠረን መኖሩን እንዴት ሊያዉቁ ይችላሉ? መጥፎ ወይም የሚመር የአፍ ጣዕም ሲሰማዎት በጣም የሚመከረዉ ዘዴ ግን የሚያምኑት ሰዉ መጥፎ የአፍ ጠረን እንደአለዎትና እንደሌለዎት እዉነቱን እንዲነግሮት መጠየቅ ናቸዉ፡፡ መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመከላከል የሚመከሩ ነገሮች/ምክሮች ምግብ ከተመገቡ በኃላ ጥርስዎትን መታጠብ(መቦረሽ) ቢያንስ በቀን አንዴ በጥርስ መካከል ያሉትን የምግብ ተርፍራፊ በጥርስ መጎርጎርያ ወይም ፍሎስ ማዉጣት ምላስዎትን መቦረሽ አርትፊሽል ጥርስ ወይም ድድ ካለዎት ማፅዳት የአፍ ድርቀትን መከላከል፡ ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ማቆም፤ዉሃ በብዛት መጠጣት(ቡና፣ለስላሳ መጠጦችና አልኮል የአፍን መድረቅ ሊያመጡ ይችላሉ፡፡

የደም ማነስ

የደም ማነስ ምልክቶች የደም ማነስ ምልክቶች እንዳለብን የደም ማነስ አይነቶች ይለያያል መነሻው, የበሽታው ከባድነት እና ማንኛውም የጤና ችግር (ክንታሮት, ቁስለት, የወር አበባ ችግር ወይም ካንሰር የመሳሰሉት) አስተዋጽዎ ያደርጋሉ. ያለብዎት የደም ማነስ ቀለል ያለ ከሆነ ወይም ከብዙ ጊዜ በፊት ከተከሰተ ምንም አይነት ምልክት ላናይ እንችላለን. ለማንኛውም አይነት የደም ማነስ የጋራ የሆኑ ምልክቶች እነሆ የድካም ስሜት እና ጉልበት ማጣት ያልተለመደ ፈጣን የልብ ምት በተለይ እንቅስቃሴ ስናደርግ የትንፋሽ ማጠር እና ራስ ምታት የትኩረት ማጣት የማዞር ስሜት የቆዳ መገርጣት የእግር ጡንቻ መሸማቀቅ የእንቅልፍ ማጣት 1- በብረት እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ በብረት እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ ያለባቸው ሰዎች የሚከተሉት ምልክቶች ሊኖሩባቸው ይችላል ባልተለመደ ሁኔታ ወረቀት, በረድና ቆሻሻዎችን ለመመገብ መፈለግ ጥፍሮቻችን ወደላይ መታጠፍ (መበላሸት) የአፍ መሰነጣጠቅ እና መቁሰል 2- በቫይታሚን ቢ 12 እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ በቫይታሚን ቢ 12 እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ የሚከተሉት ምልክቶች ሊኖሩት ይችላል በእጅና እግር ላይ መርፌ የመወጋት ስሜት መሰማት የመዳሰስ ስሜት ማጣት መንቀጥቀጥ እና ለመራመድ መቸገር የእጅና እግር መንቀርፈፍ እና መጠንከር (መገተር) የአስተሳሰብ መለዋወጥ 3- በሊድ (አመራር) መመረዝ የሚከሰት የደም ማነስ በከባድ ሁኔታ በሊድ መመረዝ ወደሚከተሉት ምልክቶች ያመራናል ሰማያዊ_ጥቁር መስመር በድድ ላይ መኖር የሆድ ህመም የሆድ ድርቀት ማስታወክ 4- በቀይ የደም ሴሎች ውድመት የሚከሰት የደም ማነስ የአይን እና ቆዳ ቢጫ መሆን ቡናማ ወይም ቀይ ሽንት የእግር ቁስለት ህፃናት እንዳይፋፉ / እንዳይዳብሩ መሆን የኩላሊት ጠጠር በሽታ አይነት ምልክቶች 5- ሲክል ሴል የደም ማነስ የሲክል ሴል የደም ማነስ ምልክቶች የድካም ስሜት ለኢንፌክሽን መጋለጥ በህፃናት ላይ የዕድገት እና ብስለት መዘግየት የመገጣጠሚያ, ሆድ, እጅና እግር በተወሰነ ቆይታ በተደጋጋሚ ከባድ የህመም ስሜት መከሰት ናቸው የደም ማነስ ህክምና 1- በብረት እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ ይህ አይነት የደም ማነስ የአመጋገብ ስርዓታችንን እና ብረት በመውሰድ ማከም ይቻላል። ይህ የብረት እጥረት የተከሰተው ከወር አበባ ውጪ በሆነ የደም መፍሰስ ከሆነ የሚፈስበትን ቦታ ማወቅ እና እንዲቆም ማድረግ ተገቢ ነው። 2- በቫይታሚን እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ ፎሊክ አሲድ እና ቫይታሚን ሲ እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ በምግብ መስተካከል ይችላል ስለዚህ በምግብዎ ውስጥ እነዚህን መጨመር ተገቢ ነው። ጨጔራችን ቫይታሚን ቢ 12 የመምጠጥ ችግር ካለበት በመርፌ መውሰድ(መወጋት) ተገቢ ነው። 3- በከባድ በሽታ የሚከሰት የደም ማነስ የዚህ አይነቱ የደም ማነስ የተለየ ህክምና የለውም የጤና ባለሙያዎች ያለብንን ከባድ በሽታ ማከም ላይ ያተኩራሉ። ምልክቶቹ እየጨመሩ የሚመጡ ከሆነ የደም ልገሳና ቀይ የደም ሴሎች እንዲመረቱ የሚያደርግ ሆርሞን በመርፌ ይሰጣል። 4- አኘላስቲክ የደም ማነስ ለዚህ ችግር ህክምና የሚሆነው የቀይ ደም ሴሎችን ቁጥር ለመጨመር የደም ልገሳ ነው። የአጥንት መቅኒ(bone marrow) ንቅለ ተከላ ሊደረግለት ይችላል። 5- በአጥንት መቅኒ ችግር የሚከሰት የደም ማነስ የዚህ በሽታ ህክምና ከቀላል መድሃኒቶች ጀምሮ ኬሞቴራፒ ወይም የአጥንት ንቅለ ተከላ ያስፈልገዋል። 6- ሄሞላይቲክ የደም ማነስ የዚህ ችግር ህክምና ችግሩን ሊያስከትሉ የሚችሉ መድሃኒቶች ካሉ ማቆም፣ ተያይዘው የሚመጡ ኢንፌክሽኖችን ማከም፣ ቀይ የደም ሴሎችን የሚያጠቃ በሽታን የመከላከያ መንገዳችንን ለመግታት መድሃኒት መጠቀም ናቸው። እንዳለብን የደም ማነስ ህመም ክብደት/ጥንካሬ የደም ልገሳ እና የደም ማጣራት ህክምና ሊደረግለት ይችላል። 7- ሲክል ሴል የደም ማነስ የዚህ አይነቱ የደም ማነስ ህክምና ኦክስጂን መስጠት፣ ህመም የሚያስታግሱ መድሃኒቶችን መውሰድ፣ በአፍና በደም ስራችን ፈሳሾች(fluid) መውሰድ ህመም ለመቀነስ ይረዳናል። 8- ታላሲሚያ የደም ማነስ ይህ የደም ማነስ በደም ልገሳ፣ ፎሊክ አሲድ መውሰድ፣ ጣፊያን ማስወገድ፣ የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ማድረግ ለማከም ይረዳናል። የአጥንት ጥንካሬ የሚሰርቁ ምግቦች ልብ ሳንል በምግብ ጉዳት ከሚደርስባቸዉ የሰዉነት ክፍሎች ውስጥ አጥንት አንደኛዉ ነዉ፡፡ አጥንት ጥንካሬ

የአይን አለርጂ

የአይን አለርጂ የሚከሰተው አይንዎ ላይ የመቆጥቆጥ ስሜት እንዲሁም የመቅላት ባህሪይ ሲሆን ይህ ችግር ህፃናትንና አዋቂዎችን ያጠቃል፡፡ዋነኛዎቹ የህመሙ መገለጫዎች የአይን መቅላትና ከአይን ፈሳሽ ሲኖር መኖር ናቸዉ፡፡የህመሙ መንስኤ፡- የአይን አለርጂ የሚከሰተዉ አለርጂዉእንዲከሰት የሚያደርጉ አለርጂኖች በንፋስ ምክንያት ወደ አይንዎ በሚገባበት ወቅት ነዉ፡፡የህመሙ ምልክቶች አለርጂዉን በሚያመጡ/አለርጂኑን ተከትለዉ የሚከሰቱ ሲሆን በድንገት የሚጀምሩ፣ወቅትን ተከትለዉ አሊያም አመቱን በሙሉ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡የህመሙ ምልክቶች፡- በብዛት ከሚታዩት የአይን አለርጂ ምልክቶች ዉስጥ የአይን መቅላት፣ዉሃ የመሰለ የአይንፈሳሽና ሁለቱንም አይን ማሳከክ ናቸዉ፡፡ሌሎቹ የህመምምልክቶች ብርሃን ሲያዩ ማቃጠልና የአይን ቆብ እብጠትመከሰት ናቸዉ፡፡ችግሩ ብዙዉን ጊዜ ሁለቱንም አይንየሚያጠቃ ቢሆንም ህመሙ በአንደኛዉ አይን ሊብስ ይችላል፡፡ ዐይንን ማሸት የህመሙ ምልክቶች እንዲባባሱ ያደርጋል፡፡ህክምና፡- ለአለርጂክ የአይን ህመም ብዙ አይነትህክምናዎች አሉ፡፡እነርሱም ዋናው መሰረታዊ የአይን እንክብካቤ ነው የማሳከክ ስሜት ቢያስቸግርዎትም ላለማከክ መጣር ወይም አርቴፊሻል እንባ መጠቀም፣ አይንዎ ላይ ቀዝቃዛ ነገር መያዝ፣ አሊያም አለርጂን ሊቀንስ የሚችል አንታይሂስታሚን ጠብታዎችን መጠቀም · አለርጂዎች በሚከሰቱበት ወቅት በተቻለዎ መጠን እራሰን ከተጋላጭነት መከላከል፡- ቤት ዉስጥ መቆየት፣አለርጂኖች በመበዙበት ሰዓታት በርና መስኮቶችን መዝጋት።

ነስር,

ነስር በሁለት ዓይነት ይከፈላል. 1- ከፊተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (ቀዳሚ ነስር) ይህ ዓይነቱ የነስር ዓይነት ከ 90 በመቶ በላይ ለሚከሰት የነስር ዓይነት ምክንያት ነው. ከፍተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣን ነስር በቀላሉ መቆጣጠር ወይንም ማቆም ይቻላል. 2- ከኋለኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (የኋላ ነስር) ይህ ዓይነቱ የነስር ዓይንት በአብዛኘው በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን ከሌላኛው የተለየ ሕክምና የሚያስፈልገው እና ውስብስብ ነው. ነስር በአብዛኛው በቅዝቃዜ ወቅት የሚከሰት ሲሆን ከ 2 - 10 ዓመትና ከ 50 - 80 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉትንም ያጠቃል. ነስርን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? በአፍንጫ ላይ ከውጭ የሚከሰት አደጋ ወይንም አፍንጫ በመጎርጎር ምክንያት በተለያዩ የሕመም ወይንም መድኃኒቶች ምክንያት ደም መርጋት አለመቻል የደም ግፊት መጨመር ጋር በተያያዘ የሚመጣ ነስር ነው. የነስር ምልክቶች ምንድን ናቸው? በአብዛኛው ደም የሚፈሰው በአንደኛው የአፍንጫ ቀዳዳ ነው. ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የደም መፍሰስ ካለ በሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች ደም ሊፈስ ይችላል. እጅግ ከፍተኛ ደም መፍሰስ ካለ ደግሞ በጉሮሮ አድርጎ በአፍ በኩል ሊመጣ ይችላል. ከፍተኛ የሆነ ድም መፍሰስ ሲኖር ራስ ማዞር, ግራ የመጋባት እና ራስ መሳት ሊያስከትል ይችላል. ነስርን እንዴት ማቆም ይቻላል? በመጀመሪያ ራስዎን ማረጋጋት ቀጥ ብለው መቀመጥ ከጭንቅላትዎ ጎንበስ ማለት (ጭንቅላትን ወደ ላይ ቀና ማድረግ የሚፈሰውን ደም ወደ ጉሮሮ ከማምጣት ባለፈ ጥቅም የለውም) ሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች በአውራ ጣትዎ እና በጠቋሚ ታትም ግጥም አድርጎ ለአስር ደቂቃ ይዞ ማቆየት በአፍ የሚመጣን ደም መትፋት ነስሩ ካቆመ በኋላ አፍንጫዎን አለመነካካት ናቸው. ከተከሰተ ነስር በኋላ ወደ ሐኪም መሄድ የሚያስፈልገው መቼ ነው? አፍንጫዎን ለ 10 ደቂቃ ያህል ይዘው ቆይተው ነስሩ የሚያቆም ካልሆነ በአጭር ጊዜ ልዩነት በተደጋጋሚ የሚነስርዎ ከሆነ ራስ ማዞር ወይንም ራስዎን የሚስቱ ከመሰለዎት የልብ ምትዎ የሚጨምር ከሆነ እና ለመተንፈስ ከተቸገሩ ደም የሚያስመልስዎ ከሆነ በሰውነትዎ ላይ ሽፍታ ከኖረ ትኩሳት ካለዎት ናቸው. ሐኪምዎን ማማከር የሚያስፈልገው መቼ ነው? በተደጋጋሚ ነስር የሚያስቸግርዎ ከሆነ ከነስር ሌላ ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች መድማት የሚኖር ከሆነ በቀላሉ የመበለዝ ምልክቶች በሰውነትዎ ላይ ከተገኙ ደምን ለማቅጠን የሚጠቅሙ መድኃኒቶችን የሚወሰዱ ከሆነ የደም መርጋትን የሚያስተጓጉሉ ማንኛውንም ዓይንት ሕመም ካለዎት የኬሞቴራፒ ሕክምና በቅርቡ ወስደው ከነበረ ነው.

ለጥርስ ህመም

ለጥርስ ህመም- የመጀመሪያ እርዳታ እርስዎ በቤቶ ሊተገብሩት የሚችሉ ምክሮች ሞቅ ባለ ዉሀ አፍዎትን መጉመጥምጥ በጥርስ መጎርጎሪያ በጥርስዎት መካካል የቀሩ የምግብ ትራፊዎችን ማዉጣት ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ የህመም ማስታገሻ መድሃኒት መዉሰድ ወደ ጥርስ ህክማና መስጫ ማዕከል መሄድ የእንፌክሽን ምልክቶች ካለዎት ለምሳሌ እብጠት ካለ፤ ምግብ ሲመገቡ ህመም ካለ፤ የድድ መቅላት ወይም ሽታ ያለዉ ፈሳሽ ካለዎት ሀኪም ያማክሩ ህመሙ ከአንድ ቀንና ከዚያ በላይ ከቀጠለ ከጥርስ ህመሙ ጋር ትኩሳት ካለዎት በአተነፋፈስዎ ላይ ወይም ምግብ ሲዉጡ ከተቸገሩ