ማይከል ጃክሰን

ማይከል ጆሴፍ ጃክሰን አሜሪካዊ ዳንሰኛ፤ የዜማ ደራሲና ዘፋኝ ነው፡፡ 

በቅፅል ስሙ ‹‹የፖፕ ንጉስ›› በማባልም ይታወቃል፡፡ 

ዝናው ከአለም ጫፍ እስከ ጫፍ ድረስ የናረ፤ ቡዙ ሽያጭ ያስመዘገበ ቁጥር 1 ዘፋኝ ነበር፡፡ 

ለ4 አስርተ ዓመታት ተወዳጅነቱ ያስመሰከረ ጥበበኛ ነበር፡፡

ትውልድ

ማይከል ጆሴፍ ጃክሰን  የተወለደው ነሀሴ 29/1958 እ.አ.አ፡፡ 

ለቤተሰቡ 8ኛ ሲሆን ከአፍሪካ አሜሪካዊ ቤተሰብ የተገኘ ነው፡፡ 

ማይከል የተወለደው በእንዲያና ቺካጎ ከተማ ነው፡፡ 

እናቱ የፒያኖ ተጫወች ስትሆን አባቱ ቦክሰኛ ነበር፡፡ 

አባቱ በትርፍ ግዜው ጊታር በመጫወት ቤተሰቡን ያስተዳድር ነበር፡፡ 

ማይከል 3 እህቶችና 5 ወንድሞች አሉት፡፡

የስራ ህይወት

ማይከል ሀ ብሎ የዝናን ጣዐም ማጣጣም የጀመረው ከወንድሞቹ ጋር በ1984 ነበር፡፡ 

መላው ቤተሰቡ አንድ ላይ በመሆን ጃክሰን ባንድ መሰረቱ፡፡ 

ከዚያች ቅፅበት ጀምሮ ማይከል የተለያዩ ክብርና ሽልማቶችን የግሉ አደረገ፡፡ 

የሚሊኒየሙ ወንድ አርቲስት፤ የክፍለ ዘመኑ የአሜሪካ አርቲስትና የሚሊኒየሙ የፖፕ አርቲስት ሽልማቶችን አሸንፏል፡፡ 

በሮክና ሮል ዘርፍም ከወንድሞቹ ጋር በ1997 እንዲሁም በ2001 ምርጥ በመባል ተሸልሟል፡፡

በ1999 ከወንድሞቹ ጋር ቮካል ግሩፕ ሽልማትና በ2002 በዜማ ደራሲነት ሽልማቶችን አገኝቷል፡፡ 

በ2010 ማይከል በዳንስ ሆል ዘርፍ ሽልማትና እውቅና አገኝቷል፡፡ 

በ2014 በብሉዝ ሆል ኦፍ ፌም እውቅና አገኝቷል (ሁለቱንም ሽልማቶች አባቱ ተቀብሏል)፡፡

ከማይከል ስራዎች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ቲለር አልበም Thriller album)፡፡ 

የምንግዜውም ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገበ አልበም ነው፡፡ 

65 ሚሊዮን ኮፒ በአለማቀፍ ደረጃ ተሸጦለታል፡፡ 

በስራ አለም ውስጥ በአጠቃላይ 750 ሚሊዮን ዶለር አግኝቷል፡፡ 

የግል ህይወት

በ1994 ማይከል ሊሳ ሜሪ ፕርስልይን በማግባት አለምን አስገረመ፡፡

ሊሳ ሜሪ ፕርስልይ የታወቂው የሮክ አንጋፋው ኤልቪስ ፕርስልይ ሴት ልጅ ነበረች፡፡

ትዳራቸው ለ2 ዓመታት ብቻ ነበር የቆየው፡፡ በ1996 ከሜሪ ጋር ተፋቱ፡፡

በህዳር 1996 ማይከል የልጅ አባት መሆኑን ገለፀ፡፡ የልጁ እናት ዴቢ ሮው ነበረች፡፡ ዴቢ ሮው ለረጅም ግዜያት ጓደኛ ነበረች፡፡

ታህሳስ 1997 ከዴቢ ጋር በሲዲኒ አውስትራሊያ ትዳር መሰረቱ፡፡

የመጀመሪያ ልጃቸው ፕሪንስ የካቲት 13/1997 ተወለደ፡፡ ሁለተኛዋ ሴት ልጃቸው ፓሪስ በ1998 ተወለደች፡፡ 

ማይከል እና ዴቢ ሮው በጥቅምት 1999 እ.አ.አ ተፋቱ፡፡

ማይከል ሰኔ 25/2009 መተንፈስ አቆመ፡፡ ይህችን አለም ተሰናበተ፡፡ አለም በማይከል ሞት ተደናገጠች፡፡

ስለሞቱ ብዙ ቢባልም የግል ዶክተሩ ዶ/ር ማሪ ለሞቱ ተጠያቂም ሆነ፡፡