ጆን ፈ. ኬኔዲ

ጆን ፈ. ኬኔዲ 35ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት፤ ፖሎቲከኛና ተወዳጅ ሰው ነበር፡፡ ኬኔዲ የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባል ነበር፡፡ ኬኔዲ በአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ታሪክ ውስጥ ልክ እንደ አብረሃም ሊንከን በሰው ነው የተገደለው፡፡

ትውልድ

ጆን ፈ. ኬኔዲ የተወለደው በግንቦት 29/1917 በማሳቹሰትስ አሜሪካ ነበር፡፡ የኬኔዲ የዘር ሀረግ የሚመዘዘው ከአይርላንድ ነው፡፡ ኬኔዲ ለቤተሰቡ 2ኛ ልጅ ሲሆን በአጠቃላይ 9 ናቸው፡፡

ኬኔዲ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን የተከታተለው በእድዋርድ ዲቮሽን ነበር፡፡

የስራ ህይወት

በአሜሪካ አየር ሀይል (1941-1945)

ጆን ፈ. ኬኔዲ በጦር ሀይል ውስጥ ስኬታማ የሚባል ህይወት አሳልፏል፡፡ የተለያዩ ሽልማቶችን በቆይታው አግኝቷል፡፡

ለአብነት ያህል የ2ኛ የአለም ጦርነት ድል ሜዳሊያ የሚጠቀስ ነው፡፡

ኬኔዲ ታለቅ ወንድሙ ፖሎቲከኛ ነበር፡፡ የወንድሙን ፈለግ በመከተል የህይወት አቅጣጫውን ወደ ፖሎቲካ በማዞር አዲስ የህይወት ምዕራፍ ጀመረ፡፡

ፕሬዝዳንትነት (1961-1963)

ጆን ፈ. ኬኔዲ ጥር 20/1961 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመረጠ፡፡ ጆን ፈ. ኬኔዲ በመጀመሪያ ንግግሩ አሜሪካዊያን ለሀገሮች እድገት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላለፈ፡፡ ‹‹ Ask not what your country can do for you; ask what you can do for your country.››

ለጠቅላለው ለአሜሪካ ህዝብ በአንድነት የሰው ጠላት የሆነውን ፡ ጦርነት፤ ረሀብ፤ በሽታ መዋጋት እንዳለባቸው አሳሰበ፡፡ 

ግድያ

ጆን ኬኔዲ የተገደለው ዓርብ ህዳር 22/1963 ዳላስ ከተማ ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ነበር፡፡ በ3 ጥይት ተመተው ሞተ፡፡ 1 ጥይት ከጀርባው፤ 1 ጥይት ጉሮሮ ላይና 3ኛው ጭንቅላቱ ላይ ነበር፡፡

የግል ህይወት

የኬኔዲ ቤተሰቦች ከቅድመ አያቱ ጀምሮ በፖሎቲካ የኖሩ ናቸው፡፡ የፖሎቲካ ህይወቱንም ከቤተሰቡ እንደወረሰ ይታመናል፡፡

ጆን ፈ. ኬኔዲ የመጀመሪያ ትዳሩን የያዘው ከጃኪዩሊን ቦኡቨር በመስከረም 12/1953፡፡ የኬኔዲ ብቸኛ ልጅ በ1957 የተወለደችው ካሮሊን ትባላለች፡፡