ኔልሰን ማንዴላ 

ኔልሰን ማንዴላ (1918-2013) ደቡብ አፈሪካዊ የፖለቲካ አቀንቃኝ ሲሆን የአፓርታይድ አገዛዝን በመቃወም ከ20 ዓመት በላይ በእስር አሳልፏል። እ.ኤ.አ በ1994 ማንዴላ የመጀመሪያው የአፍሪካ ዴሞክራሲያዊ መሪ ሆኖ ተመረጠ። እ.ኤ.አ በ1993 የኖቬል የሰላም ሽልማት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የነበረውን የዘር መድልዎ ለማስቆም ባበረከተው አስተዋፅኦ ተሸልሟል። የደቡብ አፍሪካ ዲሞክራሲያዊ አባት ተደርጐ ይወሰዳል። እንዲሁም አገሪቱ አንድ ለማድረግ ባበረከተው አስተዋፅኦ በስፋት ይደነቃል። ኔልሰን ማንዴላ በ21ኛ መቶ ክፍለ ዘመን እጅግ ከሚደነቁ የፖለቲካ መሪዎች መካከል አንዱ ነው። በተለይም የሚታወቅበት በአዲሱ አገር ይቅርታ ስለማድረግ ባደረገው አስተዋፅኦ ነው። 

ኔልሰን ማንዴላ ትራንስኬይ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እ.ኤ.አ በሐምሌ 18 ቀን 1918 ተወለዱ። ኔልሰን ማንዴላ በጦሳ ጐሳ መጠሪያ ማዲባ በመባል ይታወቃል። ማንዴላ የአካባቢው ጐሳ መሪ ቴምብ ጐሳ አባል ነው። በወጣትነቱ ኔልሰን ማንዴላ በአካባቢ ጐሳ ባሕላዊ ስነ ስርዓቶች ላይ ይሳተፍ ነበር። ሆኖም ግን ከአባቱ በተለየ ሁኔታ ሙሉ ትምህርት ተከታትሏል። ማንዴላ በፎርት ሄር ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ እና ዊትዋተርስላንድ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ተከታትሏል። ኔልሰን ማንዴላ ጐበዝ ተማሪ ሲሆን በ1942 በሕግ ዲግሪውን አግኝቷል። 

በዩኒቨርስቲው ቆይታ ኔልሰን ማንዴላ ነጭ ባልሆኑ ዜጐች ላይ የሚደርስባቸውን የዘር መድልዎ እና እኩልነት ማጣት እንዲሁም ኢፍትሐዊነት ተገንዝቧል። በ1943 የኤኤንሲ ፓርቲ ለመቀላቀል በመወሰን በአፓርታይድ ትግል እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ ጀመረ። 

በወቅቱ ከነበሩት ጥቂት የተማሩ የሕግ ባለሙያዎች መካከል አንዱ የነበረው ኔልሰን ማንዴላ በእጅጉ ይፈለግ ነበረ። ከዚህ በተጨማሪ በኤኤንሲ ፓርቲ ውስጥ ባሳየው ቁርጠኝነት ወደ ከፍተኛ የአመራር ደረጃ ተሸጋግሯል። እ.ኤ.አ በ1956 ኔልሰን ማንዴላ ከሌሎች በርካታ የኤኤንሲ አባላት ጋር ታስሮ አገርን በመክዳት ክስ ተመስርቶበታል። 

ከተንዛዛ የፍርድ ሂደት በኋላ ተከሳሾቹ እ.ኤ.አ በ1961 በነፃ ተለቀቁ፤ ሆኖም ግን ኤኤንሲ በመከልከሉ ኔልሰን ማንዴላ በአፓርታይድ አገዛዝ ላይ በጦር ኃይል የተመራ መቋቋም እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል። ይህም ለኡምኮንቶዌሲዝዌ መስረት አስተዋፅኦ አድርጓል። 

ይህ ቡድን የደፈጣ ተዋጊ ቡድን ነበር። ኡምኮንቶዌሲዝዌ በበርካታ የአፍሪካ አገራት ስልጠና በመውሰድ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተለያዩ ጥቃቶችን ማድረስ ጀመረ። 

እ.ኤ.አ በ1963 ማንዴላ እንደገና ታሰረ እና በአገር መክዳት ተከሰሰ። በዚህ ጊዜ መንግስት ማንዴላ የደቡብ አፍሪካን መንግስት ለመጣል አሲረዋል ሲል የጥፋተኛነት ውሳኔ ወሰነ። ሆኖም ግን ጉዳዩ ዓለም አቀፍ ትኩረትን በማግኘቱ እና የደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ አገዛዝ በዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ስር ጥብቅ ቁጥጥር ወደቀ። ከፍርድ ሂደቱ መጠናቀቅ በኋላ ኔልሰን ማንዴላ ረጅም ንግግር አደረጉ። በዚህ ንግግር ላይ ለዲሞክራሲ ስላላቸው እሳቤ ቁርጠኝነት ማረጋገጥ ችሏል። 

የእስር ቤት ቆይታ 

የማንዴላ የሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተቀይሮ ከ1964-1981 በኬፕታውን አቅራቢያ በምትገኝ ሮበን ደሴት እስር ቤት ውስጥ ታሰረ። እስር ቤቱ ውስጥ ሁኔታዎች በጣም አስቸጋሪ ነበሩ። ሆኖም ግን ማንዴላ ከሌሎች በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ጋር በመሆን የጠበቀ ጓደኝነት ለመመስረት እና አስቸጋሪን የእስር ቤት ሁኔታ ለመቋቋም ችሏል። 

ከዚህ በተጨማሪ እስር ቤት ውስጥ ኔልሰን ማንዴላ ከፍተኛ ስነ ምግባር ያሳይ ነበረ። እስር ቤት ውስጥ በየዕለቱ ጥናት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያደርግ ነበር። ከረጅም ጊዜ በኋላ ስለ እስር ቤት ቆይታው ሲናገር ወቅቱ ከባድ ትምህርት የተማረበት ጊዜ እንደሆነ እና እንዲያውም በጣም አስቸጋሪ ነበረ ብሏል። ማንዴላ በእስር ቤት ውስጥ ከአንዳንድ ጠባቂዎች ጋር ጓደኝነትን ለመመስረት ችሏል። ማንዴላ በሌላ ጊዜ እንደተናገረው የሚዋጋው ከአፓርታይድ ስርዓት ጋር እንጂ ከነጭ ግለሰቦች ጋር አለመሆኑን ነው።

በእስር ቤት ቆይታው ማንዴላ በመላው ዓለም ለመታወቅ በቅቷል። ማንዴላ የመጀመሪያው ጥቁር መሪ የሆነ ሲሆን በአፓርታይድ አገዛዝ ላይ ለሚደረገው ትግል እንደ አርማ ይታያል። ስለ ማንዴላ በስፋት የሚታወቀው ነገር በእስር ቤት ለረጅም ጊዜ መቆየቱ ከመላው ዓለም ማንዴላ እንዲፈታ ግፊት ይደረግ ጀመረ። በበርካታ አጋጣሚዎች ማንዴላ ከቅድመ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ነፃነት ይሰጠው ነበር። ሆኖም ግን የኤኤንሲ የፖለቲካ እሳቤዎች ከራሱ ነፃነት ለማስቀደም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። 

ነፃነት እና አዲሲቷ የቀስተደመና አገር 

ማንዴላ እ.ኤ.አ የካቲት 11 ቀን 1990 ከእስር ተፈቷል። ዕለቱ ለደቡብ አፍሪካ እና ለመላው ዓለም ትልቅ በዓል ሆኗል። ከእስር መለቀቁ ጨቋኙን የአፓርታይድ አገዛዝ ስለመገርሰሱ ምልክት ነበር። ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ረጅም ድርድሮች ይካሄዱ ነበር። ድርድሩ አብዛኛውን ጊዜ በጐሳዎች ግጭት ዙሪያ ነበረ። ሆኖም ግን እ.ኤ.አ ሚያዝያ 1994 ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው የተሟላ እና ፍትሐዊ ምርጫ አካሄደች። ኤኤንሲ 65 በመቶ ድምፅ በማግኘት ተመረጠ። ኔልሰን ማንዴላም የመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሆነ። 

ኔልሰን ማንዴላ በ1999 ከፕሬዝዳንትነት እራሱን አገለለ። በዚህ ወቅት በታቦ ኢምቤኪ ተተክቷል። በማንዴላ የመጨረሻ ዓመታት ጤና ማጣት ከሕዝብ ጋር እንዳይገናኝ አድርጐታል። ሆኖም ግን በአንዳንድ ጉዳዮች ዙሪያ ሐሳብ ይሰጥ ነበር። እ.ኤ.አ በ2003 በአሜሪካ የተመራው ጦር ኢራቅን መውረሩን አውግዟል። ከዚህ በተጨማሪ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስ ጉዳይ በዘመቻ መልክ መርቷል። 

ማንዴላ ሶስት ጊዜ ትዳር ፈፅሟል፤ ስድስት ልጆች፣ 17 የልጅ ልጆች አሉት። የመጀመሪያ ባለቤቱ ኢበሊን ኖኮማሴ ይባላሉ። ሁለተኛ ባለቤቱ ዊኒ ማንዴላ ስትሆን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በመካከላቸው በተፈጠረው ግጭት ተለያየተዋል፤ ዊኒ በሰብዓዊ መብት ጥሰት መሳተፍ ውንጀላ ይቀርብባታል። ማንዴላ ለሶስተኛ ጊዜ በ80 ዓመቱ ግራሳ ማሼልን አግብቷል። 

ኔልሰን ማንዴላ እ.ኤ.አ ታሕሳስ 5 ቀን 2013 ከረጅም ጊዜ ሕመም በኋላ በቤተሰቡ ተከቦ በ95 ዓመቱ ሕይወቱ አልፏል።