ሮዛ ፓርክስ

ሮዛ ሉዩስ ፓርክስ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና አክቲቪስት የነበረች አሜሪካዊነት ነች፡፡

በአሜሪካ ኮንግሬስ የነጻነት እናት እና ለሰብዓዊ መብት ቀዳማዊት እመቤት ተብላ ተሰይማለች፡፡

ትውልድ

ሮዛ ፓርክስ የተወለደችው በአላባማ ግዛት ሲሆን ግዜውም የካቲት 4/1913 ነው፡፡

የአፍሪካ የዘር ግንድ ያላት ስትሆን በቅድመ አያቷ በኩል የስኮት-አይሪሽ ዘርም አላት፡፡

ሮዛ በህፃንነቷ ብዙ ችግሮችን የተጋፈጠች፤ በቶንሲል በሽታና በድህነት የተጠቃች ነበረች፡፡

የስራ ህይወት

ለነጭ አልነሳም ስለ ማለቷ

ሮዛ የሙሉ ቀን ሰራተኛ ስትሆን ወደ ቤቷ የምትመለሰው ምሽት ላይ ነበር፡፡

ከዕለታት በአንዱ ቀን ዕለተ ሀሙስ ታህሳስ 1/1955 ወደ ቤቷ ለመመለስ አውቶቡስ ተሳፈረች፡፡ አውቶቡስ 2 መቀመጫ ደረጃዎች ነበሩ፤ ለነጮችና ለጥቁሮች፡፡ ከፊት የነበሩ መቀመጫዎች ተይዞ ስለነበሩ ወደኋላ ለነጮች የተዘጋጀ ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡ 

የአውቶቡሱ ሹፌር ጃምስ ብሌክ ነጭ ፈረንጅ ነበር፡፡ አውቶብሱ በሰዎች የተጨናነቀ ስለነበር በግዜው አላስተዋለም ነበር፡፡ ከቆይታ ቡኋላ ሮዛ መቀመጫዋ ላይ ተቀመጣ ሌሎች ነጮች ቁሞ እየሄዱ ነበር፡፡ በዚህ መሃል ነበር እንድትነሳ ትዕዛዝ የሰጣት መልሷ ግን እምቢታ ነበር፡፡

ሮዛ ፓርክስ ከክስተቱ ከዓመት ቡኋላ ስለሁኔታ ስትናገር ‹‹ሹፌሩ እንድነሳ ትዕዛዝ ሲሰጠኝ መላ ሰውነቴ ኩርትም አለ››፡፡

የግል ህይወት

ሮዛ ፓርክስ ለ92 ዓመታት ያህል እስከለተ ሞቷ ድረስ በዴትሮእት ስትኖር ነበረች፡፡

በጥቁር ህዝቦች ዘንድ ብቻ ሳትሆን በመላው ዓለም እንደ ጀግና የምትታይ ነበረች፡፡

በጥቅምት 24/2005 እ.አ.አ በራሷ አፓርታማ ውስጥ ሞተች፡፡

የግል ህይወት

• 1976 የDetroit ግዛት በሮዛ ፓርክስ መንገድ ሰየመ

• 1980 የMartin Luther King Jr. ሽልማት አገኘች

• 1984 የCandace ሽልማት አገኘች

• ጥቅምት 30/2005 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ወ. ቡሽ በሷ ቀብር ላይ የአሜሪካ ባንዲራ ከፍ ብሎ እንዳይብወለወል አደረጉ፡፡