አብርሃም ሊንከን በኬንተኪ ሃርዲን ውስጥ እ.ኤ.አ የካቲት 12 ቀን 1809 ተወለደ። ቤተሰቡ መካከለኛ ቤተሰብ ሲሆን ወላጆቹ የቨርጂኒያ ተወላጆች ሲሆኑ ሐብታም ወይም በጣም ታዋቂ አልነበሩ። በልጅነቱ አብርሃም እናቱን ያጣ ሲሆን አባቱም ወደ ኢንዲያና ተጓዘ።
አብርሃም እንጨት በመፍለጥ እና ሌሎች የጉልበት ሥራዎች መስራት ነበረበት። ነገር ግን ለእውቀት ባለው ጥማት በትምህርቱ ለመላቅ ጠንክሮ ይሰራ ነበር። ይህም የሕግ ባለሙያ እንዲሆን አስችሎታል። በኢሊኖይ ተዘዋዋሪ ፍርድ ቤት ለ8 ዓመታት ሰርቷል። ፍላጐቱ፣ ችሎታው እና ጠንካራ ሠራተኝነቱ በማንም ዘንድ የተመሰከረለት ነው።

ሜሪ ቶድን አግብቶ አራት ልጆችን ወልደዋል። ምንም እንኳን ሶስቱ ልጆቻቸው በልጅነታቸው የሞቱ ቢሆንም። እንደ ሕግ ባለሙያ አብርሃም ፈጣን አሳቢ እና የንግግር ችሎታ ነበረው። እ.ኤ.አ በ1854 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመረጠ።
እ.ኤ.አ በ1858 ለሕዝብ ተወካዮች/ሴነት ለመወዳደር ሞከረ ምንም እንኳን በምርጫው ባይቀናውም የመከራከር ችሎታው በሪፐብሊካን ፓርቲ ውስጥ እንዲታወቅ አስችሎታል። በ1860 አብርሃም ሊንከን የሪፐብሊካን ፓርቲ ተመራጭ በመሆን ለፕሬዝዳንትነት ተወዳደረ፤ ከጠንካራ ፍልሚያ፣ እልህ አስጨራሽ ዘመቻ በኋላ ሊንከን የመጀመሪያው የሪፐብሊካን የአሜሪካ መሪ ሆነ።
በ1861 ሊንከር ፕሬዝዳንት ሆኖ በመመረጡ የደቡቡ የአሜሪካ ክፍለ ከሰሜኑ ለመገንጠል እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመረ። አብርሃም ሊንከን የባሪያ ንግድን በመቃወም ይታወቅ ነበር። ሆኖም ግን ሊንከን የደቡቡ መገንጠል አይደግፍም ነበር። በዚህ መሠረት የአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት ተጀመረ። የእርስ በእርስ ጦርነቱ ከፍተኛው ወጪ ያስወጣ እና በርካታ ሰዎች የተሳተፉበት ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ሊንከን የጠቅላላ ሕዝቡን ድጋፍ የሚያጣበት ጊዜ ነበረ።
መጀመሪያ ላይ ጦርነቱ በደቡብ ተገንጣይ ግዛቶች እና በአንድነት አቀንቃኞች መካከል የተደረገ ጦርነት ነበር። ነገር ግን ጦርነቱ እየተፋፋመ ሲሄድ ሊንከን የባሪያ ንግድ መቆሙ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን አመነበት። ለሊንከን የባሪያ ንግድ በመሠረታዊነት ስህተት ነበር። ከአራት ዓመት ከባድ ጦርነት በኋላ የፌዴራል ኃይሎች ደቡቦችን አሸነፉ። ሊንከን የአንድነት ኃይሎችን በማዳን የባሪያ ንግድ እንዲቆም አድርጓል።
ከእርስ በእርሱ ጦርነት በኋላ ሊንከን አገሪቱን አንድ ለማድረግ ለደቡቦች የሰፈራ ቦታ ሰጣቸው። እ.ኤ.አ ጥር 31 ቀን 1965 የባሪያ ንግድ ከሕግ ውጪ እንዲሆን እና በኮንግረስ ሕግ እንዲሆን አስችሏል። የዩናዩትድ ስቴትስ ሕገመንግስት የተሻሻለው 13ኛ ሕግ እ.ኤ.አ ታሕሳስ 6 ቀን 1865 በይፋ ሕግ ሆኖ ተፈርሟል።
ግድያ
ሮበርት ኢ.ቪ እና የኮንፌደሬት ጦር ከተሸነፈ ከ5 ቀናት በኋላ ሊንከን የፎርድ ቲያትርን በሚጐበኝበት ጊዜ በጆን ዊልከስ ቡዝ ተገደለ። የሊንከን ሞት በመላ አገሪቱ ሐዘን ፈጥሯል።
ሊንከን ከአሜሪካ ተፅእኖ ፈጣሪ እና አስፈላጊ ፕሬዝዳንቶች መካከል አንዱ ተደርጐ ይወሰዳል። እንዲሁም ሊንከን የአንድነት ኃይሎችን በማዳን እንዲሁም የሪፐብሊካን ፓርቲ እሴቶችን በማስተዋወቅ አስተዋፅኦ አድርጓል። ሊንከን የሐቀኝነት እና ታታሪነትን እሳቤዎች አጣምሮ የያዘ ሰው ነበር።