አልበርት አይንስታይን

በጀርመን ሀገር በማርች 14 1879 አ.ም በጀርመን ኡልም ከተማ ተወለደ ፤ ከዛም አንደ አመት እንደሞላው መላው ቤተሰቡ ወደ ሙኒክ የተባለቸ የጀርመን ከተማ የአልበርት አባትና አጎት የመሰረቱትን የኤሌክትሪክ እቃዎቸ ማምረቻ ድርጅት ለማስተዳደር አቀኑ፤  ከ14 አመታት በኋላ ግን ድርጅቱ ሲከስር ቤተሰቦቹ በድጋሚ ወደ ጣሊያን ሲያመሩ አልበርት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን እስኪያጠናቅቅ ሙኒክ ኑሮውን ቀጠለ ፤ 

ከዛም በ16 አመቱ ስዊዘርላንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከአጠናቀቀ በኋላ በ1896 አ.ም አልበርት ለ4 አመታት የሚቆይ የሂሳብ እና ፊዚክስ የማስተማር ዲፕሎማ ትምህርት ክፍል የመመዘኛ ፈተናውን በአጠቃላይ ጥሩ ውጤት በማምጣት በተለይም ደግሞ በፊዚክስና ሂሳብ ይበልጥ የተሻለ ውጤቴ በማስመዝገብ ዙሪክ ስዊዘርላነድ ፖሊቴክኒክን ተቀላቀለ ፤  ከነበሩትም 6 ተማሪዎች ብቸኛዋ ሴት ተማሪን እና የወደፊት ባለቤቱ የምትሆነውን ሚሌቫ ማሪክን ተዋወቃት።

በ1903 አ.ም አልበርት እና ሚሌቫም ተጋቡ ፤ የመጀመሪያ ልጃቸውንም ሀንስ በማለት ሰየሙት ፤ ሁለተኛ ልጃቸውም በ1910 ሲወለድ ኤድዋርድ በማለት ስም ሰጡት ፤ ከተጋቡ 16 አመታት ካሳለፉ በኋላ ግን አልበርት እና ማሪክ ትዳራቸው ፈረሰ ፤ አልበርት ከመጀመሪያ ባለቤቱ ከተፋታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከኤልሳ ጋር ትዳር መሰረቱ ፤ በ1933 ገደማ ወደ አሜሪካ ሲያቀኑ ኤልሳ ግን የልብ እና የኩላሊት በሽታ ምክኒያት አሜሪካ ከገቡ በ3 አመታቸው አረፈች። 

አልበርት የዲፕሎማ ትምህርቱን ካተናቀቀ በኋላ ለ2 አመታት ያህል ስራ ለማግኘት ብዙ ስንገላታ ቆይቶ በ1901 አካባቢ የስዊስ ዜግነቱን አግኝቶ በበርን ከተማ ስራ ጀመረ ፤ የዶክትሬት ዲግሪውንም በ1905 ከዙሪክ ዩኒቨርሲቲ ባገኘበት አመት 4 ፈር ቀዳጅ ጽሁፎችን በማሳተም በአለም ምሁራኖች ዘንድ ስሙ እንዲገን አደረገው ፤ ከዛም እስከ 1922 አካባቢ ታላላቅ ተቁማት ውስጥ የተለያዩ የስራ ድርሻዎችን በመያዝ ሲያገግል ቆይቶ በ1921 በፊዚክስ ላበረከታቸው አስተዋጽኦዋች የኖቤል ተሸላሚ ለመሆን በቃ ፤ የአሜሪካዊነት ዜግነቱንም በ1940 ሲያገኝ አሜሪካ ለሰዎች መብት ያላትን ክብር የሰዎችን የፈጠራ ባህል እንደሚያዳብር በአድንቆ ገለጸ።   

በሂዎት ዘመኑም 300 ያህል ሳይንሳዊ ጽሁፎችን እና 150 አካባቢ ሳይንሳዊ ያልሆኑ ጽሁፎችን በማሳተም ፤ ከነዚህም መካከል ዝነኛውን E=MC2 የተባለውን የሪላቲቪቲ ንድፍ ሀሳቡን ፤ የኩአንተም ሜካኒክስ ንድፍ ሀሳብ ፤ ፊዚካል ኮሰሞሎጂ እና የእንቅስቃሴ ቀመር ከሚጠቀሱት ጥቂቶቹ ናቸው፤ በመጨረሻም በኤፕሪል 17 1955 አ.ም አልበርት ከዚህ አለም በ76 አመቱ በሞት ተለየ።

ስለዚህም የአልበርት አይንስታይን ህይወትና ሳይንሳዊ አስተዋጽኦ ይህንን ይመስል ነበር ፤ አይንስታይንም ለብዙ ትረካዎች ፤ ፊልሞች ፤ ቲያትርና ሙዚቃ ስራዎች ምክኒያት ነበረ ፤ እንዲሁም ለየት ባላው የጸጉር ስሪቱ ይበልጥ ስሙ ገኖ ይታወቅ ነበር።