
ባራክ ሁሴን ኦባማ የጥቁር ህዝቦች አንገት ቀና ያደረገ የአሜሪካ መሪ፡፡ ባራክ ኦባማ 44ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆኖ ያገለገለ ጥቁር አሜሪካዊ መሪ ነው፡፡ ልዕለ-ሀያሏን ሀገረ አሜሪካ ለ2 የፕሬዝዳትነት ግዜያት አገልግሏል፡፡
ትውልድ
ባራክ ኦባማ በነሀሴ 4/1961 እ.አ.አ በሃዋይ ግዛት ተወለደ፡፡ አሜሪካን በፕሬዝዳንትነት ከአገለገሉ ሰዎች በሃዋይ የተወለደ ብቻኛ ሰው ነው፡፡ ኦባማ የተወለደው ከነጭ እናትና ከጥቁር አባት ሲሆን የእናቱ የዘር ሀረግ የሚመዘዘው ከጀርመን ሲሆን አባቱ ኬኒያዊ ነበር፡፡
ቤተሰቦቹ የተጋቡት በየካቲት 2/1961 እ.አ.አ ሲሆን ኦባማን የወለዱት ከጋብቻ ቡኋላ በ6 ወራቸው ነበር፡፡
የስራ ህይወት
ቺካጎ የህግ አማካሪነት – በ1991 እ.አ.አ ኦባማ ለ12 ዓመታት ያህል በህግ በዩሊቨርሲቲ ኦፍ ቺካጎ በአስተማሪነት አገለገለ፡፡
ከ1997-2004 እ.አ.አ በኢሊኖእስ ግዛት ሴነተር በመሆን ለ7 አመት አገለገለ፡፡ በኢሊኖእስ ግዛት ባገኘው ሴነተርነት በመጠቀም በ2004 እ.አ.አ ለአሜሪካ ሴነተርነት ተወዳደረ፡፡ በዚህም በጥር 3/2005 እ.አ.አ የአሜሪካ ሴኔት ሆኖ ተመረጠ፡፡ ‹‹ታማኝ ዴሞክራት›› በመባልም ተገለፀ፡፡
ፕሬዝዳንት ባራክ ኦበማ
ባራክ ኦባማ በ2008 እ.አ.አ አለምን ጉድ ያሰኘውን የአሜሪካ ምርጫ ፉክክር ከጆን ማኬን ጋር በመወዳደር አሸንፎ የልዕለ-ሀያሏ አሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመረጠ፡፡
አለም ከጫፍ እስከ ጫፍ ለባራክ ኦባማ አድናቆቱን ገለፀ፡፡
ኦባማ በአላም ላይ በፈጠረው ተፅዕኖ የ2009 እ.አ.አ የኖቤል የሰላም ሽልማት ማዕረግ ለማግኘት በቃ፡፡
ኦባማ ለ2ኛ ግዜ በ2012 እ.አ.አ በመመረጥ በድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን ቀጠለ፡፡
ኦባማ በስልጣን ዘመኑ በርካተ ነገሮች ሰርቷል፡፡ ደካማ ጎኖች ከሚባሉ ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን መፍቀዱ ይጠቀሳል፡፡
ኦባማ ከሰራቻቸው ስራዎች ውስጥ የጤና ፖሊሲው በከፍተኛ ይጠቀሳል፡፡ ይህ ፖሊሲው ከ2010 እስከ 2020 እ.አ.አ የሚተገበር ነው፡፡
በ2001 እ.አ.አ ኦሳማ ቢላደንን በመግደል በአሜሪካዊያን ዘንድ እንደ ጀግና ተቆጥሯል፡፡
የስልጣን ግዜው ያበቃው በጥር 20/2017 እ.አ.አ ነበር፡፡ ከቤተሰቡ ጋር በዋሽንግተን ከተማ በመኖር ላይ ይገኛል፡፡

