እማሆይ ትሬዛ 

እማሆይ ትሬዛ (1910-1997 እ.ኤ.አ) የሮማ ካቶሊክ መነኩሴ የነበሩ ሲሆን ድሆችን እና የተገፉ ሰዎችን በመላው አለም ለመርዳት ጊዜያቸውን የሰጡ ነበሩ። በርካታ ዓመታትን በካልካታ ህንድ ውስጥ የሚሽነሪ የረድኤት ድርጅት በማቋቋም እርዳታ የሚያስፈልጓቸውን ሰዎች በመርዳት ጊዜያቸውን አሳልፈዋል። በ1979 እ.ኤ.አ እማሆይ ትሬዛ የሰላም ኖቬል ተሸላሚ ሆነዋል። እንዲሁም የበጎ አድራጎት አርአያ ለመሆን በቅተዋል። በ2016 እ.ኤ.አ እማሆይ ትሬዛ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቅድስት ትሬዛ በመባል ከቅዱሳን ተርታ ተሰልፈዋል። 

እማሆይ ትሬዛ የተወለዱት 1910 እ.ኤ.አ ኮፒ የመቄዶኒያ ሪፐብሊክ ውስጥ ነው። ስለልጅነት ጊዜያቸው ብዙም አይታወቅም ነገር ግን በወጣትነት እድሜያቸው መነኩሴ ለመሆን እንደተጠሩ እና ድሆችን ለመርዳት ፈጣሪ እንደመረጣቸው አመኑ። በ18 ዓመታቸው በአየርላንድ የመነኩሴዎች ቡድን ውስጥ ለመቀላቀል ፈቃድ አገኙ። ከጥቂት ወራት ስልጠና በኋላ ከሎሬቶ እህቶች ጋር ወደ ህንድ ለመጓዝ ፍቃድ አገኙ። መደበኛ ሐይማኖታዊ ቃለ መሐላ በ1931 እ.ኤ.አ በመፈፀም ቅድስት የሊሴክስ ቅድስት ቴሬስ የሚለውን ስም መረጡ –  ይህ ስም የቅዱሳን ሚሽነሪዎች ስያሜ ነው። 

ህንድ በደረሱበት ወቅት በመምህርነት አገልግለዋል ሆኖም ግን በካልካታ በተስፋፋው ድህነት ምክንያት “የሚሽነሪ ተራድኦ” ለማቋቋም ቻሉ። የዚህ ሚሽን ተቀዳሚ ዓላማ ረዳት የሌላቸው ሰዎችን መንከባከብ ሲሆን። እማሆይ ትሬዛ ሌሎች ሰዎችን ማገልገል ዋነኛው የክርስቶስ እየሱስ አስተምሮ መርህ መሆኑ ተሰማቸው። 

ካልካታ ውስጥ ሁለት ጊዜ አስቸጋሪ ጊዜያትን አሳልፈዋል። የመጀመሪያው ቤንጋል ውስጥ በ1943 እ.ኤ.አ ተከስቶ በነበረው ድርቅ ሳቢያ ሲሆን ፤ 2ኛው በ1946 እ.ኤ.አ የተነሳው የሂንዱ/እስልምና ብጥብጥ ነበር። 

ይህም የሆነው ሕንድ ከመገንጠሏ በፊት ነው። በ1948 እ.ኤ.አ በካልካታ ድሆችን ለመርዳት የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ሆኑ። መልበስ የሚወዱት የህንድ ሳሪ ፣ ጠርዙ ሰማያዊ የሆነ ቀሚስ የሕንድ ባህላዊ ቀሚስ ነው። 

ለበርካታ ዓመታት እማሆይ ትሬዛ እና ጥቂት የሂንዱ እና ሌሎች መለኩሴዎች በቀን ውስጥ አነስተኛ መጠን ያለው ገቢ እና ምግብ እያገኙ አብዛኛውን ጊዜ ገንዘብ ለማሰባሰብ ይጠቀሙበት ነበር። ነገር ግን ቀስ በቀስ ለድሆች ያላቸው ፍቅር እና እንክብካቤ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ እየተደነቀ ላቸው እና በህንድ ፖለቲከኞችም ጭምር እየተወሰላቸው መጣ። 

በ1952 እ.ኤ.አ የመጀመሪያውን ቤት ሕይወታቸው ለሚያልፍ ሰዎች አዘጋጁ ይህም ቤት ቢያንስ ሰዎች በሚሞቱበት ጊዜ በክብር እንዲሞቱ ለማድረግ የተዘጋጀ የመጀመሪያው ቤት ነው። እማሆይ ትሬዛ አብዛኛውን ጊዜ ሕይወታቸው ለማለፍ ጫፍ ላይ ከደረሱ ሰዎች ጋር ጊዜያቸውን ብዙ ጊዜ ማሳለፍ ይወዳሉ። አንዳንዶቹ ተገቢው የህክምና ትኩረት ስለማይሰጣቸው እና ህመም አስታጋሽ መድሐኒቶችንም ማግኘት አይችሉም ሲሉ ይተቿቸዋል። ሌሎቹ ግን በሰው የተረሱ ሰዎችን በሚሞቱበት ሰዓት እንኳን የመንከባከብ እድል መስጠታቸውን ያደንቁላቸዋል። 

ሥራቸው በመላው ዓለም ተስፋፋ በ2013 እ.ኤ.አ በ130 አገራት የሚሰሩ 700 ሚሽኖች ነበሩ። የሥራቸው ስፋት ወላጆች የሞቱባቸውን ልጆች እና የማይድን በሽታ የያዛቸውን ሰዎች ማካተት ጀመረ። 

እማሆይ ትሬዛ ሌሎች ሰዎች እምነታቸውን እንዲቀይሩ ለመስበክ ሞክረው አያውቁም። በእርሳቸው የእንክብካቤ ድርጅት ውስጥ ማንኛውም ሰው የራሱ እምነት እንደጠበቀ ይቆያል። ሆኖም ግን እማሆይ ትሬዛ በካቶሊክ ሐይማኖት የጠበቀ እምነት አላቸው። በዚህም መሰረት ውርጃ ፣ የሞት ቅጣት እንዲሁም ፍቺን – ምንም እንኳ በዓለም ውስጥ ታዋቂ ሳይሆኑ ጀምሮ በጥብቅ ይቃወማሉ።  

በ1979 እ.ኤ.አ የሰላም የኖቬል ሽልማት “ድህነትን እና ማጣትን ለማሸነፍ ትግል ውስጥ ባበረከቱት አስተዋጽኦ ከውጪ ተሸልመዋል።” ነገር ግን እማሆይ ትሬዛ በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ አልተገኙም ነገር ግን ከሽልማቱ የተበረከተላቸውን 192,000.00 ዶላር ለድሆች እንዲሰጥ ጠይቀዋል። 

እማሆይ ትሬዛ በአንድ ወቅት የአለምን ሰላም እንዴት ማምጣት እንደሚቻል ተጠይቀው ነበር እሳቸው ሲመልሱ “ወደ ቤታችሁ ሂዱ እና ቤተሰቦቻችሁን ውደዱ”  አሉ። 

ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት እማሆይ ትሬዛ በበርካታ የጤና ችግሮች ሲሰቃዩ ቆይተዋል። ነገር ግን ይህንን ድሆችን እና ያጡ ሰዎችን የመርዳት ተልዕኳቸውን አላቋረጡም ነበር። በመጨረሻዎቹ ጥቂት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ኒውዮርክ ብሮንክስ ውስጥ ከልዕልት ዲያና ጋር ተገናኙ። ሁለቱም የሞቱት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው። 

የእማሆይ ትሬዛን ሞት ተከትሎ ቫቲካን ስለእርሳቸው መልካም ስራ የማስዋብ እንቅስቃሴ በመጀመር እርሳቸውን ቅድስት አድርገው ለመሰየም ሁለተኛውን እርምጃ ወስደዋል። እማሆይ ትሬዛ በጥቅምት 2003 እ.ኤ.አ በዳግማዊ ፖፕ ጆን ፖል በመደበኛነት ቅድስት ሆነዋል።