
ሄነሪ ፎርድ አሜሪካዊ የብዝነስ አብዮተኛና የፎርድ መኪና አምራች ባለቤት ነው፡፡
ፎርድ የአውቶሞቢል ቀመር ያገኘ ሰው ሳይሆን በብዙ አሜሪካዊያን የምትመች የአመረት ሰው እንጂ፡፡
ትውልድ
ሄነሪ ፎርድ በሀምሌ 30/1863 እ.አ.አ በሚቺጋን ተወለደ፡፡ ፎርድ በአባቱ በኩል አይርላንዳዊ ሲሆን እናቱ የቤልጂዬም ዘር ያለባት አሜሪካዊ ነች፡፡
የፎርድ ቤተሰቦች ሀብታም የነበሩ ሲሆን አጎቶቹ የሀገርቷ ሀብታሞች ውስጥ የሚመደቡ ናቸው፡፡
ፎርድ በሳምንቱ መጨረሻ 4 ማይል ያህል ርቀት እየተጓዘ ቤተክርስቲያን መሄድ ፀሎት ይፈፅም ነበር፡፡
የስራ ህይወት
በ1891 እ.አ.አ ፎርድ በእንጂነሪንግ ተመርቆ ኤዲሰን የተባለ ካምፓኒ ውስጥ ተቀጠረ፡፡
ከ2 አመት ቆይታ ቡኋላ ዋና እንጂነር በማደግ ገንዘቡንና ግዜውን ወደራሱ ጥናት ማድረግ ገባ፡፡
በዚህም ጥረቱ በ1896 እ.አ.አ በራሱ የሚሰራ መኪና ለመስራት በቃ፡፡
የመጀመሪያ ሙከራውን በሰኔ 4/1896 እ.አ.አ አደረገ፡፡
ሄነሪ ፎርድ ከማልኮምሶን ከተባለ ጓደኛው ጋር በመሆን በሰኔ 16/1903 እ.አ.አ ፎርድ ሞተርስ ኩባንያ አቋቋሙ፡፡
የመጀመሪያ ስራቸውን በጥቅምት 1/1908 እ.አ.አ አስተዋወቁ፡፡
ፎርድ ህልሙ ሩቅ ነበር፡፡ በመጀመሪያው የአለም ጦርነት ከአውቶሞቢል አምራችነት ወደ አውሮፕላን አምራችነት ተሸጋገረ፡፡
በፎርድ ኩባንያ ውስጥ በፕሬዝዳትነት ሲያገለግል የነበረው ልጁ ኤደሴል ፎርድ በግንቦት 1943እ.አ.አ አረፈ፡፡ ሄነሪ ፎርድ የፕሬዝዳንትነትን ስልጣን ለመውሰድ ወነሰ፡፡
ፎርድ የ161 የፈጠራ ባለቤትነት ያለው ሰው ነው፡፡
የግል ህይወት
ሄነሪ ፎርድ ክላራ ጄንን በሚያዝያ 11/1888 እ.አ.አ አገባ፡፡ ፎርድ የአንድ ልጅ አባት ነበር፡- ኤደሴል ፎርድ ይባላል፡፡

