ማሀትማ ጋንዲ

ማሀትማ ጋንዲ በህንድ ፖለቲካዊ የነፃነት እንቅስቃሴ የነበረው ዋነኛ መሪ በ1869 አ.ም ፖርባንዳር ተወለደ። የእናቱም ሀይማኖታዊ ታማኝነት ለጋንዲ ባህሪ ዘላቂ ተጽኖ አዋለበት ። ጎበዝ ተማሪ የነበረው ጋንዲ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን እየተከታተለ አባቱ በሞት ሲለዩ ጉዞውን ወደ ኢንጊሊዝ ሀገር አድርጎ በህግ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያዘ። 

በዛም ጊዜ መጽሀፍ ቅዱስን አጥንቶ በእየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ትህትና አና ምህረት የሚሉት ሀሳቦች ተጽዕኖ አሳደሩበት ። በ1883 አ.ም የ13 አመቱ ጋንዲ የ14 አመቷን ካስቱረባይን አግብቶ ። የመጀመሪያ ልጃቸው ከተወለደ ከጥቂት ቀናት በኋላ ቢሞትም ። የ4 ወንድ ልጆች አባት ለመሁን በቃ።  

የህግ ትምህርቱን አጠናቆ ወደ ህንደ እንደተመለሰ ወዲያውኑ ወደ ደቡብ አፍሪካ የህግ ትምህርቱን ስራ ላየ ለማዋል አመራ። ጋንዲም ደቡብ አፍሪካ በነበረው ህንዶች ላይ በሚደርሰው መድሎና ህገ-ወጣዊ ሁኔታዎች በጣም አዘነ ። በመቀጠል የመጀመሪያውን የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደ ። 

ደቡብ አፍሪካም ለ21 አመታት ቆይቶ በ1915 አ.ም ወደ ህንድ ተመለሶ የእራስ ማስተዳደርን ሀሳብ በመያዝ የህንድ ብሄራዊ አንቅስቃሴ መሪ ሆኖ መስራት ጀመረ ። ጋንዲ ተከታታይ ሰላማዊ ሰልፎችን በስኬት ሲያካሂድ ኢንጊሊዝ ሰልፎቹ ሰላማዊ ስለነበሩ ለመከልከል አልቻሉም። 

ጋንዲ ተከታዮቹን ውስጣዊ ስነ-ስርአት እንዲያዳብሩ ያበረታታቸው ነበር። ከሌሎች ብሄራዊ አንቅስቃሴ አባላት የሚያጋጨው የነበረው አንዱ ሀሳብ ኢንጊሊዝን በሀይል ከስልጣን ለማውረድ ከሚሻው አባል ሱብሀስ ቻንድራ ይጠቀሳል ። ጋንዲም በተደጋጋሚም ሰላማዊ ያልሆኑ ሰልፎች እንዳይካሄዱ ይከለክል ነበር። 

በ1930 አ.ም በጋንዲ መሪነት የኢንጊሊዝን አስተዳደር ህግ በመጣስ ወደ ባህር የሚያመራ ሰልፈ ተካሄደ ። በመቶዎች የሚቆጠሩም ተከታዮች ታሰሩ በተጨማሪም የተወሰኑ ህንዶች ኢንጊሊዛውያንን በመግደላቸው ጋንዲ ሰልፉ አንዲቋረጥ አስተላልፎ ህንድ ለነጻነት ዝግጁ አለመሆኗን ገለጸ። 

ጦረነቱ ካበቃ በኋላ ኢንጊሊዝ ህንድን ነጻነቷን አንደምትሰጣት አወጀች ። ኢንጊሊዝ ግን ህንድን ለሁለት ለመክፈል ስትወስን ጋንዲ ሀሳቡን በጥብቅ ተቃውሞ ሙስሊሞችና ሂንዱዎች ተቻችለው በሰላም መኖር እንደሚቸሉ ለማሳየት ሞክሮ ሳይሳካለት ቀረ ። ህንድ ወደ ሂንዱ እምነት ተከታዮች ሚበዛባት ህንድ እና ወደ እስልምና እምነት ተከታዮች ሚበዛባት ፓኪስታን ተከፈለች ። ጋንዲም ቀኑን በሀዘን አሳለፈ። 

በተጨማሪም ጋንዲ ከፖለቲካው ራቅ ብሎ በሂንዱ የካስት ወይም የዘር ክፍፍል ስርአትን አጥብቆ ይቃወም ነበር ። በተለይም የማይነኩት በሚባሉት ዘሮች ላይ ይደርስ በነበረው ፅዩፍ አመለካከትን ለማስወገድ በርካታ እንቅስቃሴዎችን ቢያካሂድም ከማህበረሰቡ ብዙ ተቋዋሚዎች ለዘመናት የነበረውን የዘር ክፍፍል ስርአት እንዲቋረጥ ስላልፈለጉ የጋንዲን ሰብአዊ ጥረቶች ዋጋ አሳጧቸው። 

በ78 አመቱ በተጨማሪ የሀይማኖት ግድያዎችን ለመከልከል ባደረገው ጥረት ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች የእርስ በእርስ ግድያን ለማቆም በተስማሙበት 10ኛ ቀን የሂንዱ አባል በነበረው ብራህሚን የጋንዲ ለሙስሊሞችና ለማይነኩት ዘሮች ያደርግ የነበረውን ሰብአዊ ትግል ባለመደገፉ የህዝቡ አባት በመባል ሚጠራው የነጻነት መሪ ማሀትማ ጋንዲን በመግደል ከህዝቡ ነጠቃቸው።