
አውስትሪያኑ የነርቭ ህክምና ስፔሻሊስት የነበረው ሲግመንድ ፍሮይድ በሜይ 6 1856 አ.ም በፍሪበርግ በጊዜው የአውስትሪያ ግዛት የአሁኗ ቼክ ሪፐብሊክ ተብላ በምትጠራው ከተማ ተወለደ። ልጅነቱንም በሊፕዚግ እና ቪየና እያሳለፈ ቆይቶ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በጣም ጥሩ ዉጤት አስመዝግቦ ። በተለይም በተለያዩ የአውሮፓ ቋንቋዎች የተለየ ችሎታው ይታወቃል ። በ17 አመቱ ፍሮይድ በቪየና ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ክፍል በፍልስፍና ። በፊዚዮሎጂ እና የእንስሳት ትምህርት ክፍሎች ላይ ለመማር ተቀላቀለ።
በ1881 አ.ም ትምህርቱን አጠናቆ በቪየና አጠቃላይ ሆስፒታል በስነ-አእምሮ ክሊኒክ ክፍል እየሰራ በጎን የምርምር ስራውን ቀጠለ ። ከነዚህም ምርምሮች ኮኬን ሚባለውን አደንዛዝ ዕጽ አእምሮ ላይ ሚያደርሰውን ጉዳትና ለእምሮአዊና ሰውነታዊ ችግሮች መፍትሄነት ያለው ጥቅም እና የአፌዚያ ጥናቶች ይጠቀሳሉ። በቪየና አጠቃላይ ሆስፒታል ከ5 አመታት ቆይታ በኋላ የግሉን በነርቭ ህክምና ላይ ያተኮረ ክሊኒክ ከፍቶ መስራት ጀመረ ።
ከዚያም በ1886 አ.ም ከማርታ በርኔስ ጋር ተጋብቶ ስድስት ልጆችን ወልደው ይኖሩ ነበር ። ፍሮይድ ያበረታታው የነበረው ስልት ታካሚዎች ውስጣቸው ታምቆ ያለውን ሀሳብና ስሜት እንዲገልጹ ነበር ። በመጀመሪያም ሂፕኖሲስን ቀጥሎም በቀዳሚነት ሚታወቅበት ትራንስፈራንስን በመጠቀም ነበር ። በመቀጠልም ፍሮይድ በይበልጥ ለሚታወቅበት ሳይኮአናሊስስ ሀሳብ ላይ ለመድረስ በነበረው ጉዞ የራሱን ህልሞች ። መንፈሳዊ ጭንቀቶች እና ስሜቶችን ይጠቀም እንደነበር ይገልጻል።
በ1899 አ.ም የህልሞች ትንታኔ የሚል መጽሀፍ አሳትሞ። በጊዜው የነበሩት የህልም ፍልስፍና ሀሳቦችን በመንቀፍ የበለጠ ትኩረት ለራሱ ሀሳብ “ህልሞች ያልተሳኩ ምኞቶች ማሳኪያ” እንደሆነ ገልጸ ። በተጨማሪም ሌሎች በስነ-አእምሮ እና ወሲባዊ ፍልስፍና ላይ ያተኮሩ ስራዎችን አቀረበ።
በተጨማሪም ለፍሮይድ መላምት መሰረታዊ የነበረው ንቃተ ህሊና ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜም የንቃተ ህሊና ሀሳብ የተዋወቀው ከተጨቆኑ ሀሳቦች ጋር ሲሆን የተጨቆኑ ሀሳቦች ማለት አእምሮአችን ውስጥ ኖረው ግን ከንቃተ ህሊና የተወገዱ ሲሆኑ በተወሰኑ ሁኔታውች ላይ ጎልተው ሊታዩ ሚችሉ ናቸወ በማለት ገልጾታል።
ሌላው ፍሮይድ ይታወቅበት የነበረው ፍልስፍና የስነ-ወሲባዊ ዕድገት ላይ ያተኮረው ኦዴፒየስ ኮምፕሌክስ ይባላል ። ይህም ሀሳብ ሚገልፀው ልጆች ከተቃራኒ ጾታ ወላጃቸው ጋር የወሲብ ግንኙነት መፈጸም እንደሚፈልጉ የተጨቆነ ሀሳብ አላቸው በማለት እነዚህንም የአእምሮ ሆኔታውች ለሶስት በመክፈል ኢድ ፣ ኢጎ እና ሱፐር ኢጎ በማለት ገለጻቸው።
ዝነኛ በነበረው ሳይኮአናሊስስ ሀሳቡ በ20ዎቹ ክፍለ ዘመን ይበልጥ ተቀባይነት አግኝቶ ለወደፊቱም የአእምሮና ባህሪ ታካሚዎች ላይ ለውጥ ለማምጣት ይጠቀሙበት የነበረው የፍሮይድን ሀሳብ መሰረት በማድረግ ነበር ። ሌሎች ደግሞ ተቃራኒ የህይወት አንጻፊና ሞት አንጻፊ ሀሳብ እንዲሁም በተጨማሪ በሀዘንና በመንፈስ ጭንቀት መሃል ያለውን ልዩነት ለሚገልፀው ሀሳቦቹ ፍሮይድ ይታወቅ ነበር።
ሲግመንድ ፍሮይድ በ83 አመቱ ብዙ አመታት ከማጨስ ባደረሰበት የአፍና ጉሮሮ ካንሰር ምክኒያት ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

