ፈሊጣዊ አባባሎች
ለጉንዳን ደም የለው ለገንዘብ ቤት የለው
ነገር ሲበዛ ይሆናል ዋዛ
ቁራ ሲነጣ አህያ ቀንድ ያወጣ
ትንኝም ለሆዱ ዝሆንም ለሆዱ ወደ ወንዝ ወረዱ
ሀሳብ ከፊት አይፈታ ሙት አይመታ
ለሚመለከት ለሚያየው ሞት ቅርብ ነው
ይቺ ባቄላ ያደረች እንደሆን አትቆረጠምም
ያልወለደ አጋድሞ አረደ
ሁል ጊዜ ከመደንገጥ አንድ ጊዜ መሸጥ
ለሰው ጠላቱ ይወጣል ከቤቱ
እዳውን ከፍሎ የከተተ ጌታውን የተሰናበተ
ስራ ያጣ መለኩሴ አደገኛ ቦዘኔ ተባለ
የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ
ደብተራ የዘኬ ጎተራ
ከህጻን ጋር አትብላ ድንች ድንቹን ይለቅምብሀል
ተቅበላ ጥጋብ የስቅለት ጦም ማደር ይሻላል
ውሻ የጌታውን ጌታ አያውቅም
ነገር በነገር ይጠቀሳል እሾህ በእሾህ ይነቀሳል
እኔው ሞቼ እኔው ቄስ ጠርቼ
የላሜ ልጅ ያውራዬ ውላጅ
ያላባቱ ቢዛቁን አባክኖ ያባክን
ቀን ይነዳ እንደ ፍሪዳ
ያንቺን አትበይ ገንዘብ የለሽ የሰው አትበይ ምግባር የለሽ
የሚሰርቀውን ያጣ ሌባ ሰላማዊ መስሎ ይገባል
እድሜ ያልመከረው ሽማግሌ ከውሀ የገባ አሞሌ
ሀሰት ስለበዛ እውነት ሆነ ዋዛ
ከአህያ የዋለች ሳር መጋጥ ትማራለች
ሆድ የኔ ነው ሲሉት ቁርጠት ሆኖ ይገድላል
ሆድ ያበላውን ያመሰገናል
መልክ ታጥቦ አይጠጣ ወይ አይበላ
የዘሬን ብለቅ ይቆማምጠኝ አለ ቆማጣ
የልጅቷን ስጋ በእናቷ ቅቤ
ስም ያለው ሞኝ ነው
ብልህ ሚስት ለባሏ አክሊል ናት
የለመደ ፈረሰኛ ዛብ አይጨብጥ እርካብ አይረግጥ
የፈሳ የጥጋብም አይደል ሲረሳ
ቅምሙ የበዛበት ወጥ አይፋጅ አይኮመጥጥ
ሰው ያስገድላል አባይ ውሀ ያስጮሀል ድንጋይ
ሹምና ጥጥ እያደር ይከዳል
ነገርን በእርቅ ወይፈንን በድርቅ
ጥልቅ ብዬን ውሀ ወሰዳት
ዝም ያለ ተንኮለኛ ይመስላል እንብላ ያለ ስስታም ይመስላል
ሰውን ማመን ቀብድ ተቀብሎ ነው
ቀለም ሲበጠበጥ ብርእ ሲቀረጥ
የሽሮ ድንፋታ እንጀራው እስኪመጣ ነው
ዱላን ይዞ ሌባን መጠየቅ
ያበደ ለኑሮው የፈረደ ለጉሮሮው
እኩሉ በዶሮ እኩሉ በሽሮ
ውስጥ ውስጡን ድመትም አውሬ ነች
ከኑግ ጋር የተገኘ ሰሊጥ በጣም ይጣፍጣል
የልጅ እናት አባይ ናት
ጸሀይ የጠዋት አዱኛ የሽበት
ትንሽ ጭላንጭል ታስይዛለች ምንጭር
ሺ ዝንብ መሶብ አይከፍትም
ለእሳት እንጨት ካልነፈጉት አይጠፋም
እንደ መረብ ሸፍኖ እንደ እንቁላል ደፍኖ
ዝሆን እንሆ ፍለጋው ወዴት
ለሰው እንግዳ ላገሩ ባዳ
ለሴት ጠላ ለፈረስ ቆላ
ሀረጉን ሳብ ዛፉ እንዲሳሳብ
ዛፍ በሌለበት እንቧጮ አድባር ይሆናል
ያንበሳ ማላጅ ጋማ ይዞ ጅብን መውጋት አህያን ተጎዝጉዞ
እንኳን ለእህቴ ለሌላውም ይዘፍናል አንገቴ
እውር ሲወበራ በሸማው ላይ አራ
ጤፍ ከአቅሙ እንክርዳድ ከፈለ
ያልተሾመ አያዝ ያልቀሰሰ አያናዝዝ
የሚያማ ጠበኛ ዘወር ይበል ከኛ
ፈሷን ፈስታ ቂጧን ጨበጠች
ለአንበሳ አታበድር ካበደርክ አትጠይቅ
ድግርና ገባር ሲተካከል ያምር
ቁቅም ከፈስ ተቆጠረች
የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷ ጸጉር ታየ
ቆቅ ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ
ተሞተች ሚስቴ ምን አለኝ ካማቴ
ጀምበር ሳለ እሩጥ አባት ሳለ አጊጥ
ጥቂት ያለው ሁሉ ብርቁ ነው
ነጋዴ ወረቱን ዘላን ከብቱን ገበሬ ምርቱን
የሚሰራ ምንም አያወራ
ያለአንድ የላት በዘነዘና ትነቀስ
ለተሾመ ይሟገቱለታል ለተሻረ ይመሰክሩበታል
ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ
ሲስሟት እንቢ ብላ ሲጎትቷት
የነቶሎ ቶሎ ቤት በሊዝ ተሸጠ
ቸኩሎ ከተጠቀመ ዝግ ብሎ የተጎዳ ይሻላል
ፈረሰኛ የወሰደውን እግረኛ አይመልሰውም
ሁለቱን የተመኘ አንድም አላገኘ
ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት ከቡሄ ወዲያ የለም ክረምት
የማታድግ ውርንጫ እናትዋን ትመራለች
Nisthu, [1/12/2024 10:29 AM]
አማርኛ አባባሎች:
ያባቱን ቢሰጡት ህይወቱ ያባቱን ቢነሱት ሞቱ
ላሊበላ አደራውን አይበላ
እንዳትሄድ ቀየዳት እንዳትበላ ለጎማት
ሲያውቀኝ ናቀኝ
ሆሆሆ ስቄ ልሙት አለ ሰውየው
ቆርሶ ያላጎረሱትን ቀዶ ያላለበሱትን ብላቴና ማዘዝ አይገባም
ሲቸኩሉ የታጠቁት ለወሲብ አይመችም
ጅብ እማያቁት አገር ሄዶ ቴሌ ሴንተር ከፈተ
ወንዝ ለወንዝ ሩዋጭ የሰው በግ አራጅ
ለመሀን እምዬ ለአገልጋይ እትዬ ብርቋ ነው
ሀሰተኛ ብርቱ ወንጀለኛ
ለጋስ ቢለግስ አበደረ እንጂ እንዲያው አልሰጠም
ለትኋን ልጓም ማጉረስ ላፈኛ ሰው መመለስ አይቻልም
ንጉስ በመንግስቱ ጎልማሳ በሚስቱ አምላክ ባምላክነቱ
ተልባ መስሎሽ ሰናፍጭ ትቀምሽ
ሴት ከጠላች በቅሎ ከበላች አመል አወጣች
የሚያስፈራውን ለሚነግርህ የሚያስቀዝነውን ንገረው
ሀብታም በገንዘቡ ድሀ በጥበቡ እርስ በርስ ይቃረቡ
ነገር ሲያመልጥ እራስ ሲመልጥ አይታወቅም
እድላም አሞሌ በዶላር ይሸጣል
ፈሪ የናቱ ልጅ ነው
የሀምሌ ጭቃ ቅቤ ለጋ
መልክ ታጥቦ አይጠጣ ወይ አይበላ
ቀድሞ የሸተውን ወፍ ይበላዋል ቀድሞ የሚናገረውን ሰው ይጠላዋል
ሹም ለሹም ያወርሳል ጉም ተራራ ያለብሳል
ነቢያት በቀየሱ ሀዋርያት ገሰገሱ
የገበያ ሽብር ለሌባ ሰርጉ ነው
ዝንብ ሳያቆሙ ዝግን አይቅሙ
ያምራል ብለው ከመናገር ይከፋል ብሎ መተው
ባለጌ ያለዉ ቻት ሩም እሾህ ያለዉ አሳም ነገሩም ልዋጥህ ቢሉት እሺ አይልም
እንጀራ ይጋግሩዋል እማድ ቤት መላ ያማክሩዋል ለሴት
ለገላጋይ ደም የለውም
ያለ ይበዛል አለ ወፍጮ
ፈጣሪን የሚያህል ጌታ ርስትን ያህል ቦታ
እንደ ጸሀይ የሞቀ እንደ ጨረቃ የደመቀ እንደ አበባ ያሸበረቀ
ፍጥም አፍራሽ ቤተክርስቲያን ተኳሽ
ያሞሌ ጥጃ በወንዙዋ ትነፋ
ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም
የሞኝን ጠላ በለው በአንኮላ
ድሀ ሲቀልጥ አመድ አመድ ይሸታል
ለዘመዴ ያዝናል ሆዴ
ልጅና ጦጣ ውሀ ይጠጣ
ለፍየል ስም አውጣ ቢለው ሞት አይደርስ አለው
ዘመድን የሚወጉበት ጦር ጀንፎው አይለቀቅም
ለምን ያለው ስልቻውን ጫን ያለው ኮርቻውን አያጣም
ፈጅቶ ከሚያጠግበኝ እስኪበርድ ይራበኝ
ታለቀ መቆጠብ ተሞተ መንጠብጠብ
ተሟጋች – እኔ እረታ ይመስለኛል ሰውም ይመለከተኛል
እጅና ጭራ አፍና እንጀራ
ዘር የጣቴ ምድሩ ያባቴ
የማይሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል
ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም
እንደ ንብ ቀስሞ እንደ ወጥ ቀምሞ
ቀኑ የጨለመበት መንገዱ ዘንግ ነው
ሁለት ቁና ሰጥቼ አንድ ጥንቅል
የወደቀ ዛፍ መንገዱን ዘጋ
ሴትና ዶሮ ሳያብድ አይውልም
ያልበላህን አትከክ
ተዋሰኝ ግዝት ይሆነኝ አበድረኝ አይማረኝ
የማይሰራ አይብላ የማይረዳ አይጥላ
ባለጌን ከወለደ የገደለ ጸደቀ
የጨጌ ከብት በየወገኑ ይከተት
ላለፈው ክረምት ውሀ ማቆር አይቻልም
የዝንጀሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ
ፈትል ሲረዳዳ አንበሳ ያስራል
ዶሮ በልቶ ከብስና ጎመን በልቶ በጤና
ችኩል አፍ ሞትን ይጠራል
ሆዳም ቢፈተፍት የጠገበ ይመስለዋል
ይመሰክረዋል ለነፍሱ ይፈተፍተዋል ለከርሱ
ያረረበት ያማስል
ሴት የላከው ሞት አስፈራራው
ለምን ሰርግ ይሄዳል ሰርግ አለ በቤቱ
ተሁለት ዛፍ የወደቀ
የ10 አለቃዬ ምክትሌ ሆይ አንተም እንደ መቶ ትኮራለህ ወይ
የማን እርሻ ብለህ እረስ የማን ሚስት ብለህ ውረስ
ለወታደር ሰፊ መንደር ለወዲላ መልካም ዱላ
ይብራና ይብራ ተጣሉ በሰው ሽንብራ
ትላንት ልጄን ዛሬ እናቴን ምን ይበጃል ዘንድሮ አለ አውራ ዶሮ
ሳይከካ ተቦካ
ሰውን ሰው ናቀው የራሱን ሳያውቀው
ሹመት ሲገኝ ዘመድ አይገድም
ቶፋ መቀበሪያው ያው ፈፋ
ሀይለኛ ዱቄት ከነፋስ ይጣላል
ያህያ እንግዳ የጅብ እራት ነው
ሁሉም ከኋላው ያገኘዋል እንደስራው
ለመስማት የፈጠንህ ለመናገርና ለቁጣ የዘገየህ ሁን
እጅና አፍ አይተጣጡም
የምህረት ጎደሎ የባሪያ ወይዘሮ
ለጨቅጫቃ ሰው ከማበደር ይሻላል በጄ ማደር
ዝንብ ቢሰበሰብ መግላሊት አይከፍትም
እብድና የዘመኑ ፖሊስ ህግ አያቅም
ዘመን የሚወልደውን ንጉስ የሚፈርደውን የሚያውቅ የለም
Nisthu, [1/12/2024 10:29 AM]
አማርኛ አባባሎች:
ትምህርት ከሚሉት ነቀርሳ ኤድስ ከሚሉት በሽታ ያውጣን
ቁርጥ ያጠግባል ተስፋ ያታልላል
እንጣጥ እንደ ፌቆ ሙልጭ እንደ ስብቆ
ቀን ከህዝብ ሌት ከጅብ
ተሌባ ሌባ ቢሰርቀው ምን ይደንቀው
ለንፉግ ሰው የገበያ መንገድ ይጠበዋል
የሴት ምክር የሾህ አጥር
የፈሪ ዱላ አያዳግምም
ነቅናቂ ሳለ ማን ጥሩ ይጠጣል
ታሳጭ ማራኪ ይሻላል
የሴት ምክር የሾህ አጥር
ስምሽ ማነው ሲሏት ቂጤ ትልቅ ነው አለች
የፈሪ በትር አስር
የሎሌ አልቃሽ የሴት ቀዳሽ የቄስ አውደሽዳሽ
ሽማግሌና ጅብ በላላባት ይገባል
ቡና እና ማሽላ እየሳቀ ያራል
ነገረኛ ዝንጀሮ ውሻ ታረባለች
ይህንን ፈርቼ ደጄን በቀን ዘግቼ
መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይውላል
ሀብታም ያለ ድሀ አይኮራም ድሀ ያለ ሀብታም አይበላም
ውስጥ ውስጡን ድመትም አውሬ ነች
የፈቷት ሴት ያጠቡት ወጪት የወጡበት ቤት አንድ ነው
የቀን ጠማማን ሚዳቆ አትዘለውም
ትንቢት ይመራል ልጓም ይገራል
ለውጠኝ ባይ የሚሻለውን አውቆ
ለሆዴ ጠግቤ በልብሴ አንግቤ
ሽሮ ቢደነፋ እንጀራ እስኪቀርብ ነው
ዝሆን ቢያንቀላፋ ዛፍ ተደግፎ ነው
ተሰብሮ ቢጠገን እንደድሮው አይሆን
ሀሜት አይቀር ከድሀም ቤት
ውሀ በብልሀት ይቆላል በእሳት
ሴት ሲያፏጩላት ያረሱላት ይመስላታል
ባለጌን ከወለደ የገደለ ጸደቀ
ዝምታ ራሱን የቻለ መልስ ነው
እውር ምን አይቶ ደንቆሮ ምን ሰምቶ
ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል
ሹመት ላወቀው ይከብደዋል ላላወቀው ያሳብደዋል
ከኛ ወዲያ ጎራሽ እህል አበላሽ
ጸጸት እያደር ይመሰረት
እግረ ቀጭን ይሞታል ሲሉ እግረ ወፍራም ይሞታል
ችኩል ቅቤ ያንቀዋል
የዘንድሮውስ ብርድ ቆማጥ ያሳቅፋል
የልጅ ተሟጋች በፊት ሰማይ ያያል ኋላ መሬት
በአህያ ቆዳ የተሰራ ድንኳን ጅብ ሲጮህ ይፈርሳል
ሰነፍ ሴት ያገባ በሬው በሰኔ ገደል የገባ
ካለቃና ከጠገራ ፊት ዞር በል
ባጎረስሁኝ ጣቴን ተነከስኩኝ ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ
ወዛም ገማ ቢለው የነጭ ወሬ ነው አለው
ለድሪ ያሉት አንገት ለአሸንክታብ
የተለጎመ በሬ ከቀንበሩ ቢያመልጥ ቢላዋ ይጠብቀዋል
እንኳን ተልባ ሽቶሽ እንዲያም ዘጠኝ ቂጣ ትፈጃለሽ
እንጀራ ምን ይጨርሰዋል መጉረስ
ደም ከውሀ ይቀጥናል
የሚያፈስ ቤት ጨቅጫቃ ሚስት
የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ
ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት
ፈረስ በራሪ በቅሎ ሰጋሪ
በጠራ ተሻገር በተሳለ ምተር
ለጠጪ ሰው የመጠጥ ወሬ አውራው
የሚወዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ
ውል ያዋውላል ታንኳ ያሻግራል አቧራ ያስላል
ካልታዘልኩ አላምንም አለች ሙሽራ
ይቅደም ደግነት ይከተል ቸርነት
ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ
ፈረስ ሲያጠብቅ ልጓም አይለቀቅ
የተናጠ ወተት ቅቤ ይወጣዋል
ንጉስ በዘውዱ ድሀ ባመዱ
ያየ ልናገር ቢል የሰማ ላውራ አለ
እንደ እንቁላል ድፍን እንደ መረብ ሽፍን
እንደ አጤ ስርአት እንድ አብርሀም እራት
ለእውር ዝማሜ ለመላጣ ጋሜ
ያልጋ ሴሰኛ ሶስት ያስተኛ
እንባ ሲሻኝ አይኔን ጢስ ወጋኝ
ያልበላኝን ቢያከኝ አይገባኝ
ባልና ሚስት ከአንድ ባህር ይቀዳል
የፈሪ ገዳይነት ለማታ
ነገር በእርቅ መንገድ በድርቅ
የመንገድ ዳር እሸት ባል የሌላት ሴት ለማንም ናት
ዳቦ ያለ ቅርፊት ጠላ ያለ ምርጊት
ነገሩ ነው እንጅ ቢላዋ ሰው አይጎዳም
ያልሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል
እንግዳ ሲያዘወትር ቤተሰብ ይሆናል
ፍቅር ፍቅር ሲሉ ደሀ ሆነው ቀሩ
ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ጌታና ሎሌ ተሟግቶ የማይሆን ነው ከቶ
Nisthu, [1/12/2024 10:29 AM]
አማርኛ አባባሎች:
ውል አያወላውል ምላት አያሻግር
እናትዋን አይተህ ልጅቷን አግባ
እንዲያው ብትመለሺ የገንፎ እንጨት ላሺ
የሚያልቅ እህል ከማያልቅ ዘመድ ያጣላል
ባልና ሚስት ሊተዋወቅ የሰርገኛ ልብ ይውለቅ
ያመኑት ፈረስ ጣለ በደንደስ
የማያደርግ እንትን ከቤተክርስቲያን ይቆማል
የምበላው ሳጣ ልጄ ጥርስ አወጣ
ዱርዬ ያገባ በሬው በሰኔ ገደል የገባ
ሰካራም ቤት አይሰራም
ጥጃ ቢፈነጭ በሜዳ ውሀ ቢሮጥ በጎድጓዳ
ነገሩ ነው እንጅ ጩቤ ሰው አይጎዳም
እናት ትረገጣለች እንደ መሬት
ድስት ግጣሙን አያጣም
ብርድ ቢያብር ለቁርጥማት ይዳርጋል
ሰው መሳይ በሸንጎ
እንጎቻ የበላ ከራት ይታገሳል
ዝም ያለ ተንኮለኛ ይመስላል እንብላ ያለ ስስታም ይመስላል
ያባት ያምራል የባእድ ያናግራል
ለዋንጫ ቡሽ ለውሀ ጉሽ የለውም
የሌባን ጠበቃ ደርበህ ውቃ
ዘመድና መድሀኒት በተቸገረ ቀን ይፈለጋል
ተዋጊ በሬህን ተናካሽ ውሻህን ያዝ
ፈጣሪን የሚያህል ጌታ ርስትን ያህል ቦታ
ከአፍ የወጣ ቃል ከእጅ የወደቀ እንቁላል
ልብ ካላየ አይን አይፈርድም
ሳይቃጠል በቅጠል
መሞት የፈለገ ግልገል ቀበሮ ቤት ሄዶ ይጨፍራል
ብልህ ሚስት ለባሏ አክሊል ናት
ወንድ ባለ በእለት ሴት ባለች በዓመት
ድሀ በሽታ አያውቅም ሀብታም ጤና የለውም
ለወጡም እዘኑለት ከደረቁም ብሉለት
ዝንጀሮ ሰው ነበር ይላሉ ድሮ
ሀምሌን በብጣሪ ነሀሴን በእንጥርጣሪ
የባልቴት ወብራ የክረምት ብራ
ያለ የሚኖር ይመስላል የሞተ ያልነበረ ይመስላል
ውል ያዋውላል ታንኳ ያሻግራል
ያኩራፊ ምሳ እራት ይሆነዋል
ዶሮ በማሰሮ ገደል ለዝንጀሮ
እንግዲህ ነገሬን በከንፈሬ
ሆድ ለማታ በልቶ ለጠዋት
ዘመድና እሳት በሩቅ
ቁጥቋጦም ሲያድግ ዛፍ ይሆናል
ለአዋጅ ነጋሪት ለጥጥ ልቃቂት
ያለ ስራ መብል ያለዳኛ ውል
የሚያብረቀርቅ ሁሉ ወርቅ አይደለም
ላያዘልቅ ጸሎት ለቅስፈት
እንብዛም ብልሀት ያደርሳል ከሞት
ሴቱ ሲበዛ ጎመን ጠነዛ
ዘመዱን ያማ ገማ
የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ
ልግመኛን መምከር ውሀ በወንፊት ማኖር
ያህያ ውሀ ጠጭ ሳይታወቅ መጣጭ
ሁሉም ያልፋል እውነት ብቻ ይተርፋል
ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል
ጳጉሜ ሲወልስ ጎተራህን አብስ
እንደ ጴጥሮስ ብጽላሎተ ርእስ እንደ ጳውሎስ በዘፈረ ልብስ
ተከብሮ ያደርጋል ደንቆሮ
ይብራና ይብራ ተጣሉ በሰው ሽንብራ
ታጥቦ ጭቃ
ሲስሟት ትታ ሲስቧት
የፍቅር ጣእሙ ተቃቅፈው ሲተኙ
እገሌ የዋለበት ሸንጎ አይጥ የገባበት እርጎ እርጎውንም ለውሻ እርሱንም ለውርሻ
ውሻ በቀደደው ድመት ተከተለች
ይህ አንበሳ ደም ደም አገሳ
ያህያ ስጋ ውርደተኛ አልጋ ላይ ቢያኖሩት እመሬት ይተኛ
የሚክድ ሰው አደራ ቢያስቀምጡት እጅ ይነሳል
ቢጠሩሽ አትሰሚ ቢጠቅሱሽ አታዪ ረጋ ብለሽ ሂጂ ብር ብር አትበዪ
ትምህርትን ለፈጠረ ጥይት በርጫን ላገኘ ገነት
የለመደ መደመደ
ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለእዳ አይሽከመውም
ሆዱን ያለ ሆዱን ተወጋ
እንኳን ለገንፎ ለሙቅም አልደነግጥ
እውነትና ሀቅ እያደር ይጠራል እንደ ወርቅ
የሞተን አትርሳ የወደቀን አንሳ
ለመማር ክፍል መግባት ለመኮረጅ ካሮት መብላት
የሴት ጉልበት ምላሱዋ
ና ያሉት እንግዳ እራቱ ፍሪዳ
ተቀማጭ የሌለው ተሟጋች ስልቻ የሌለው ቧጋች
Nisthu, [1/12/2024 10:29 AM]
አማርኛ አባባሎች:
የማያመሽ ባል ቅንድብ ይስማል
ሴትና ድመት ወደ ሞቀበት
እናቴ ቤት ጠላ እጠጣለሁ ብላ የቤቷን ውሀ ትታ ወጣች
ዝንብ ሩቅ አይበር የሜዳ ልጅ ዱር አይደፍር
እኔው ተቀርድጄ እኔው ተቀቅዬ ባወጣሁት ነፍስ ተንጎራደደብኝ ባለ ዘጠኝ ልብስ
እግዜር ሲስጥ እንጀራ በወጥ
ድንጋይ ለረገጠ ፍለጋ የለውም ውሀ ለጠጣ ሽታ የለውም
ባለጌን ካሳደገው የገደለው ይጽድቃል
ተናግሮ ያጣ ሰው ሶስት ጊዜ ሞቱ ነው
የጨርቅ ነጩ የበራ ልጩ
እውር ተመሪው ሞኝ ተመካሪው
በቅሎ ግዙ ግዙ አሞሌ ላያግዙ
ሚስጥርህን ለባእድ ለምን አዋየኸው ወንፊት ወሀ ይዞ የት ሲደርስ አየኸው
የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው
የልጅ ሞት የእግር እሳት
የሚሰርቀውን ያጣ ሌባ ሰላማዊ መስሎ ይገባ
የፈቷት ሴት ያጠቡት ወጪት የወጡበት ቤት አንድ ነው
እንግዳና ሞት በድንገት
ቅቤ ይፍሰስ ከገንፎ አይለፍ
ሁለተኛ ጥፋት ከገበያ ቆሞ ማንቀላፋት
ጀርባዬን አሳከከኝ ተንጠራርቼ ማከክ ተሳነኝ
ያህያ ፍለጋና የጥሬ እራት በግዜ ነው
ድል የባለ እድል
ለይቶት አባ ንጉሷ
ቁም ነገረኛ መምሰል የተለመደ አመል
ተለጣጭ የጎረቤቷን ድልህ አሟጣጭ
የማይመቱት ልጅ ቢቆጡት ያለቅሳል
ውሀ ጭስና ክፉ ሴት ሰውን ያባርራሉ ከቤት
ለሞኝ ንገረው ምን ይሰማ ብዬ ለብልህ ንገረው ምን ይሳተው ብዬ
የሌባ መኝታው አመድ መታሰሪያው ገመድ
የነቶሎ ቶሎ ቤት ግርግዳው ጭራሮ
ስራ ያጣ ቄስ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል
ያልወለድኩት ልጅ አባባ ቢለኝ ሆዴን ባርባር አለኝ
ደብር ለላስታ ድግድግታ ለጌታ
ያበደ ለኑሮው የፈረደ ለጉሮሮው
ነገር ካንሺው ስጋ ከጠባሺው
ወስፌ ቢለግም ቅቤ አይወጋም
ተኳሽ በሁለት አይኑ አያነጣጥርም
ያልሞተና ያልተኛ ብዙ ይሰማል
ያልተገራ ፈረስ ይጥላል በደንደስ
ቂጡን የተወጋ ውሻ እንደልቡ አይጮህም
ጅብ የኔ ነው ስለው ወናፌን ቀማኝ
የመኮንን ልጅ በከተማ የድሀ ልጅ በውድማ
ያንበሳ ልመና ጋማ ይዞ የቄስ ልመና አናዞ
ሴት ካላበለች ባልዋን ትወልዳለች
ለምኖ ለማኝ ቆቤን ቀማኝ
ሀብታም በመመጽወቱ ድሀ በጸሎቱ
መሄጃ የሌለው መውጫውን ያበስራል
ትንሽ ጭላንጭል ታስይዛለች ምንጭር
ባጎረስሁኝ ጣቴን ተነከስኩኝ ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ
ንጉስ ያላቸው ንቦች ማር ይበላሉ ንጉስ የሌላቸው ዝንቦች ጥንብን ይልሳሉ
የሙት ቀናተኛ ሚስቴን አደራ ይላል
ውል አያወላውል ምላት አያሻግር
ያልሰማ ጥኑ ነው ባልሽ ወዳጄ ነው
ያለውን ካልሰቱ በስም አይበሉ
ካንጀት በላይ ፍቅር እያደር ያቃቅር
የሚውል ሆድ ማለዳ ያረግዳል
የሚዳቋ ብዛት ለውሻ ሰርግ ነው
ሴትና መሬት የማይችሉት የለም
ታሳጭ ማራኪ ይሻላል
ለንፉግ ሰው የገበያ መንገድ ይጠበዋል
ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል
የሚያጠግብ ቂጣ ከምጣዱ የሚወጣ ጥጃ ከገመዱ
ያንጎርጓሪ ጉልበት የተራጋጭ ወተት
ኧረ ሳቄ ናልኝ ጥርሴስ አመሉ ነው
ያ በሬ ባገደደ ያ በሬ ገደል ገባ ያበጠው ይፈንዳ
ያገር ልጅ የማር እጅ
የማያውቁትን መስራት ከጥቅሙ ጉዳቱ ይብስ
ሸምበቆ በመርዘሙ ምሰሶ አይሆንም
ድርብርብ እንደ ደጋ ንብ
የማይዘልቅ ማህበር በጠጅ ይጀመራል
ሀብታም ያለ ድሀ አይኮራም ድሀ ያለ ሀብታም አይበላም
እድል የሌለው የሚለፋው ለሰው
ለሰው ብሎ ሲያማ ለኔ ብለህ ስማ
ናዳ መጣልህ ቢሉት ተከናንቤአለሁ አለ
ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ እከክ በፈጀው
እውርን እውር ቢመራው ተያይዞ ገደል
የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩትን ያህል ይስቃል
ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ሎሌና ጌታ ተሟግቶ
ሆድና ግንባር አይሸሸጉም
ሁሉም በየዘርህ ቢሉት አከንባሎ ጋጣ ገባ
የሞኝ ገበሬ እርሻ በሰኔ
ሴት ለቤት ወፍጮ ለዱቄት
ጳጉሜ ሲወልስ ጎተራህን አብስ
ለሰው ቢነግሩት ለሰው
እውር ምን አይቶ ደንቆሮ ምን ሰምቶ
ሰው ጥራ ቢሉት እራሱ መጣ
ለዳኛ የነገሩት በርጥብ ያቃጠሉት
ቆንጆና እሸት አይታለፍም
የማይሰማ ሰው ልቤን አፈረሰው
Nisthu, [1/12/2024 10:29 AM]
አማርኛ አባባሎች:
ከባለቤቱ (በላይ) ያወቀ ቡዳ ነው
ብልጥ ሲለግም አመድ በዱቄት ይለውጣል
እየታጠቡት ያድፋል እየመከሩት ያጠፋል
ጅብ ከላይ ውሀ ሲጠጣ ከታች ያለችውን አህያ አታደፍርሽብኝ አለ
ለሰባቂ ጆሮህን አትስጠው
ይውጋሽ ብሎ ይማርሽ
የጫማ ጠጠርና የእንጀራ ልጅ እያደር መቆርቆሩ አይቀርም
ለላም የሳር ለምለም
ድሀ ሲንቀባረር ያለቀሰ ይመስላል
ሰኔ መቃጠሪያ ህዳር መገናኛ
በወተት ላይ ውሀ መጠጣት ያበዛዋል ያነጣዋል
ቁፍ ቁፍ አሰኘሽ እንደቄብ ዶሮ ለመከራ ላሳርሽ ኖሮ
የለማኝ ስልቻ ሲንከባለል ከለማኝ እጅ ይወድቃል
ለሰይጣን አትስጠው ስልጣን
ሸማኔ በድሩ ጠይብ በመንደሩ
ሀብታም በወርቁ ድሀ በጨርቁ
ዘፍኖ አያምር እንኳን አልቅሶ
ተይዛ ትዘፍን ጦጣ
ከጦጣ የዋለ ጉሬዛ እህል ፈጅቶ ገባ
እግዜር ሲጥል እናት አታነሳም
የማይሰራ አይብላ የማይረዳ አይጥላ
ብላ ያለው ቀርቦ ተሽከም ያለው ተከማችቶ ይጠብቀዋል
ሆዴ ሆዴ የሚለውን ጌታ ያየዋል አይኔ አይኔ የሚለውን ሰው ያየዋል
የሚያብረቀርቅ ሁሉ ወርቅ አይደለም
ፈጭታ የነበረች ላመልማሎ ኮራች
ሀሜትና ጅራት በስተኋላ ነው
ብቀጥንም ጠጅ ነኝ
ድሀ በጉልበቱ ባለጸጋ በሀብቱ
የገንዘብን ነገር ካሰላሰሉት አባ ሀናም ሞቱ እንደጨበጡት
ነገሩ ነው እንጅ ጩቤ ሰው አይጎዳም
ክረምትና ወላድ ሲጠሉት ያከብራል
የሙሽራ እድሜ ቢያጥር የሰርጉ ድግስ ሆነ ለተዝካር
ተናግሮ ከማሰብ ተከንፈር መሰብሰብ
ለአፍ ዳገት የለውም
ታልጠገቡ አይዘሉ ካልዘለሉ አይሰበሩ
ለወጥ የሚሻል ቅልውጥ
ካልፈላ አይገነፍል ካልተጣደ አይበስል
ጆሮውን ቢቆርጡት መስሚያው ይቀራል
ዳኛ ሲያዳላ በዳኛ አህያ ሲያጋድል በመጫኛ
ትንሳኤ ትንሳኤ ቢሉኝ ጸሎተ ሀሙስ መሰለኝ
ነገር ለሰሚ ውሀ ለሎሚ
ነገር ሲያመልጥ እራስ ሲመልጥ አይታወቅም
ሆድ የኔ ነው ሲሉት ቁርጠት ሆኖ ይገድላል
ሀሰተኛን ሲረቱ በወንድም በእህቱ
ያለባለቤቱ አይነድም እሳቱ
ደመና በሰማይ የጨዋ ልጅ በአደባባይ
የረጋ ወተት ምርጫ ይደገምለታል
ሰነፍ ቢመክሩት ውሀ ቢወቅጡት
የሴት አገሩዋ ባሏ ማደሪያዋ አመሏ
ፈረሱም ይኸው ሜዳውም ይኸው
ችኮ የጦም ስጋ
እናቱ የሞተችበትና ገበያ የሄደችበት እኩል አለቀሱ
ይህን ፈርቼ ደጄን በቀን ዘግቼ
የልቡን አድራጊ አይናደድም
የማይመስል ነገር ለሴት አትንገር
ቀልደኛ ገበሬ ሲያስቀን አደረ
ለንጉስ የማይገዛ ለእግዚአብሄር አይገዛ
የተናጠ ወተት ቅቤ ይወጣዋል
የፍየል ጅራት ከብርድ አያድን አፍረት አይከድን
ያላሰብከውን አግኝ መረገመም ምርቃን አይደል
ቂል ሲረግሙት የመረቁት ይመስለዋል
ሀሰትና ስንቅ እያደረ ያልቅ
ነገር ካንሺው ስጋ ከጠባሺው
የአባይን ልጅ ወዳቂ የዞማ ልጅ ሳቂ
ዘመድ ቢረዳዳ ችግርም ባልጎዳ
ሽማግሌን ከምክር ከመለየት ከምግብ መለየት
ያፍላ የለው ቀርፋፋ
ለውጡኝ ባይ የሚሻለውን አውቆ
ሁሉም በየዘመድህ ቢሉት አክንባሎ ጋጥ ገባ
ሁለት ጊዜ በላህ ተፋህ
ጅል ስለላ ላይ ሄዶ ምግብ ቢቀርብለት ስለላ ላይ ነኝ ብሎ .እርፍ
እግዜር በትር ሲቆርጥ ቆላ አይወርድም
ለሹመት ያደለው የለማኝ አለቃ ይሆናል
ጅብ ከላይ ውሀ ሲጠጣ ከታች ያለችውን አህያ አታደፍርሽብኝ አለ
ውሻ በበላበት ይጮሀል
ዳር ሲፈታ መሀል ዳር ይሆናል
የማይፈርስ ምሽግ የለም
ለቅናት የለውም ጥናት
ዝንጀሮ እንሳሳቅ ካልሽ ነዶዬን መልሽ
ጥጃ ቢፈነጭ በሜዳ ውሀ ቢሄድ በጎድጓዳ
ከጠጅ ወዲያ አስካሪ ከባለቤት ወዲያ መስካሪ
ያልታደለ በረዶ ከድንጋይ ላይ ያርፋል
የለመነ ያገኛል የነገደ ያተርፋል
ያልፋል እስኪያልፍ ያለፋል
ባለፈ ክረምት ቤት አይሰራም
እናቲቱን አይተህ ልጅቷን አግባ
ቁራ ስሙን የጠራ
ለብልህ አይነግሩ ለድመት አያበሩ
ያለ ሴት ምን ያደርጋል ቤት
ያባይ ምልክቱ አንደበቱ የገዳይ ምልክቱ ሽልማቱ
ማሽላ እየፈካ ያራል
ድሪያ የዝሙት ዋዜማ
የሚሞት ልጅ አንገቱ ረጅም ነው
